1 ሳሙኤል 20:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)34 ዮናታንም በታላቅ ቁጣ ከግብሩ ላይ ተነሣ፤ አባቱም ዳዊትን ስላዋረደው ወሩ በገባ በሁለተኛው ቀን ምግብ አልበላም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም34 ዮናታንም በታላቅ ቍጣ ከግብሩ ላይ ተነሣ፤ አባቱም ዳዊትን ስላዋረደው ወሩ በገባ በሁለተኛው ቀን ምግብ አልበላም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም34 ዮናታንም በቊጣ ከማእዱ ላይ ተነሣ፤ በዚያ ቀን ማለትም አዲስ ጨረቃ በታየችበት በዓል በሁለተኛ ቀን ምንም ምግብ አልበላም፤ ሳኦል ዳዊትን በማዋረዱ ምክንያት ስለ ዳዊት ሁኔታ ዮናታን በብርቱ አዝኖ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)34 አባቱ በእርሱ ላይ ክፉ ነገርን ሊያደርግ ስለ ቈረጠ ዮናታን ስለ ዳዊት አዝኖአልና እጅግ ተቈጥቶ ከማዕዱ ተነሣ፤ በመባቻውም በሁለተኛው ቀን ግብር አልበላም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)34 አባቱ ዳዊትን ስላሳፈረው ዮናታን ስለ ዳዊት አዝኖአልና እጅግ ተቆጥቶ ከሰደቃው ተነሣ፥ በመባቻውም በሁለተኛ ቀን ግብር አልበላም። ምዕራፉን ተመልከት |