1 ሳሙኤል 20:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናታንም፥ “ይህስ ካንተ ይራቅ! አትሞትም! እነሆ፤ አባቴ ትልቅም ይሁን ትንሽ ማናቸውንም ነገር አስቀድሞ ሳይነግረኝ አያደርገውም። ታዲያ አባቴ ይህንንስ ለምን ይደብቀኛል? እንዲህስ አይሆንም!” ብሎ መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናታንም፣ “ይህስ ከቶ አይሁንብህ፤ አትሞትም! እነሆ፤ አባቴ ትልቅም ይሁን ትንሽ ማንኛውንም ነገር አስቀድሞ ሳይነግረኝ አያደርገውም። ታዲያ አባቴ ይህን ለምን ይደብቀኛል? ነገሩ እንዲህ አይደለም” ብሎ መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናታንም “ይህንንስ ከአንተ ያርቀው! አትሞትም፤ ትልቅም ሆነ ትንሽ አባቴ ከእኔ የሚሰውረው ነገር የለም፤ ይህንንም ነገር ቢሆን አባቴ ከእኔ አይሰውርም በፍጹም አይደረግም!” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንም፥ “ይህንስ ያርቀው፤ አትሞትም፤ እነሆ፥ አባቴ አስቀድሞ ለእኔ ሳይገልጥ ትልቅም ሆነ ትንሽ ነገር ቢሆን አያደርግም፤ አባቴስ ይህን ነገር ለምን ይሰውረኛል? እንዲህ አይደለም” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንም፦ ይህንስ ያርቀው፥ አትሞትም፥ እነሆ፥ አባቴ አስቀድሞ ለእኔ ሳይገልጥ ትልቅም ትንሽም ነገር ቢሆን አያደርግም፥ አባቴስ ይህን ነገር ለምን ይሰውረኛል? እንዲህ አይደለም አለው። |
ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፤ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።
በማደሪያው ፊት ለፊት ካለው ከአምላካችን ከጌታ መሠዊያ ሌላ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለእህል ቁርባን ለሌላ መሥዋዕትም የሚሆን መሠዊያን የሠራነው በጌታ ላይ በማመፅ ጌታንም ዛሬ መከተልን ለመተው በማለት እንደሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።”
ሕዝቡ ግን ሳኦልን፥ “ለእስራኤል ይህን ታላቅ ድል ያስገኘ ዮናታን መሞት ይገባዋልን? ይህ አይሆንም! ዛሬ ይህን ያደረገው በእግዚአብሔር ርዳታ ስለ ሆነ፥ ሕያው ጌታን! ከራስ ጠጉሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም” አሉት። ስለዚህ ሰዎቹ ዮናታንን ታደጉት፤ እርሱም ከመሞት ዳነ።
ከዚህ በኋላ ዳዊት በራማ ካለችው የራማዋ ከናዮት ሸሽቶ ወደ ዮናታን በመሄድ፥ “ምን አድርጌአለሁ? ምን በደልስ ፈጸምሁ? አባትህ ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልገውስ በፊቱ ምን ተገኝቶብኝ ነው?” ሲል ጠየቀው።
ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ምስክር ይሁን! ነገ በዚህ ሰዓት ወይም በሦስተኛው ቀን፥ ስለ አንተ መልካም አስተሳሰብ ያለው መሆኑን አባቴን ጠይቄ ከተረዳሁ በኋላ፥ ስለዚሁ ጉዳይ የሚገልጥልህ መልእክተኛ እልክብሃለሁ፤
ዳዊት ግን፥ “በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አባትህ በሚገባ ያውቃል፤ እርሱም በልቡ፤ ‘ዮናታን እንዳያዝን ይህን ማወቅ የለበትም’ ብሏል፤ ነገር ግን ሕያው ጌታን! በነፍስህ እምላለሁ! በእኔና በሞት መካከል አንድ እርምጃ ብቻ ቀርቷል” ብሎ ማለ።