1 ሳሙኤል 19:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ሜልኮል የጣዖት ምስል ወስዳ በአልጋው ላይ አጋደመችው፤ በራስጌውም የፍየል ጠጉር አኖረች፤ በልብስም ሸፈነችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሜልኮል የጣዖት ምስል ወስዳ በዐልጋው ላይ አጋደመችው፤ በራስጌውም የፍየል ጠጕር አኖረች፤ በልብስም ሸፈነችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የቤተሰቡን ጣዖት ወስዳ በአልጋ ላይ አጋደመችው፤ ከፍየል ጠጒር የተሠራ ትራስም በራስጌው አኑራ በልብስ ሸፈነችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሜልኮልም ተራፊምን ወስዳ በአልጋ ላይ አኖረችው፤ በራስጌውም ጕንጕን የፍየል ጠጕር አደረገች፤ በልብስም ከደነችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሜልኮልም ተራፊምን ወስዳ በአልጋ ላይ አኖረችው፥ በራስጌውም ጉንጉን የፍየል ጠጉር አደረገች፥ በልብስም ከደነችው። |
የላይሽን ምድር ሰልለው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ለወንድሞቻቸው፥ “ከእነዚሁ ቤቶች በአንዱ ኤፉድ፥ ተራፊም፥ የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት እንዳለ ታውቃላችሁን? እንግዲህ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ዕወቁበት” አሏቸው።
ካህኑ ለጦርነት ከተዘጋጁት ስድስት መቶ ሰዎች ጋር በቅጥሩ በር ላይ ቆሞ ሳለ፥ ምድሪቱን ለመሰለል መጥተው የነበሩትን አምስት ሰዎች ወደ ቤቱ ውስጥ በመግባት የተቀረጸውን ምስልና ኤፉዱን፥ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል ወሰዱ።