Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 31:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ላባም በጎቹን ለመሸለት ሄዶ ነበር፥ ራሔልም የአባትዋን ቤት ጣዖቶች ሰረቀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ላባ በጎቹን ሊሸልት ሄዶ ሳለ፣ ራሔል የአባቷን ቤት የጣዖታት ምስል ሰረቀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ላባ በጎች ሊሸልት ሄዶ ስለ ነበር፥ እርሱ በሌለበት ራሔል በቤት የነበሩትን የአባቷን ጣዖቶች ሰርቃ ሄደች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ላባ ግን በጎ​ቹን ለመ​ሸ​ለት ሄዶ ነበር፤ ራሔ​ልም የአ​ባ​ቷን ጣዖ​ቶች ሰረ​ቀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ላባ ግን በጎቹን ለመሸለት ሄዶ ነበር ራሔልም የአባትዋን ተራፌም ሰረቀም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 31:19
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም ሜልኮል የጣዖት ምስል ወስዳ በአልጋው ላይ አጋደመችው፤ በራስጌውም የፍየል ጠጉር አኖረች፤ በልብስም ሸፈነችው።


የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፤


አሁንም የአባትህን ቤት እጅጉን ናፍቆሃልና ሂድ፥ ነገር ግን አምላኮቼን ለምን ሰረቅህ?”


የባቢሎን ንጉሥ ምዋርቱን ያምዋርት ዘንድ በመንታ መንገድ ላይ በሁለቱ መንገዶች ራስ ላይ ቆሞ ነበር፤ ፍላጾችን ወዘወዘ፥ ከተራፊምም ጠየቀ፥ ጉበትም ተመለከተ።


ስለዚህ ያዕቆብ ለቤተሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፦ “እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ አስወግዱ ንጹሐንም ሁኑ፥ ልብሳችሁንም ለውጡ፥


ራሔልም ተራፊምን ወስዳ ከግመል ኮርቻ በታች ሸሸገች፥ በላዩም ተቀመጠችበት። ላባም ድንኳኑን ሁሉ ፈለገ፥ አንዳችም አላገኘም።


አምላኮችህን የምታገኝበት ሰው ግን እርሱ ይሙት፥ የአንተ የሆነውም በእኔ ዘንድ ይገኝ እንደሆነ በዘመዶቻችን ፊት ፈልግ፥ ውሰደውም” አለ። ያዕቆብ ራሔል እንደ ሰረቀቻቸው አያውቅም ነበር።


ስለዚህም ሚካ የሠራቸውን ጣዖታት፥ የእግዚአብሔር ቤት በሴሎ በነበረበት ጊዜ ሁሉ አቆሙ።


ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘አባቶቻችሁ፥ የአብርሃምና የናኮር አባት ታራ፥ አስቀድመው በወንዝ ማዶ ተቀመጡ፤ ሌሎችንም አማልክት አመለኩ።


ያዕቆብም ለመሄድ ማቀዱን ሳይነግረው ሶርያዊውን ላባን ከድቶ ኮበለለ።


እርሷም አባትዋን፥ “ፊትህ ለመቆም ስላልቻልሁ አትቆጣብኝ፥ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛልና” አለችው። እርሱም ፈለገ፥ ነገር ግን ተራፊምን አላገኘም።


ዐመፅ እንደ ሟርተኛነት ያለ ኃጢአት፥ እልኸኝነትም እንደ ጣዖት አምልኮ ያለ ክፉ ነገር ነው፤ አንተ የጌታን ቃል ንቀሃልና እርሱም ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል።”


ሊቀ ካህናቱ ሒልቂያ በቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈው ሕግ ሁሉ ተፈጻሚነት እንዲኖረው በማሰብ፥ ንጉሥ ኢዮስያስ ከኢየሩሳሌምና ከሌላውም የይሁዳ ከተማ ሁሉ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ሁሉ የቤተሰብ አማልክትን፥ ጣዖቶችንና ሌሎችንም አረማዊ የአምልኮ መፈጸሚያ ዕቃዎችን ሁሉ አስወገደ።


ነገር ግን ወደ አባቴ ቤት ወደ ወገኔም ሂድ፥ ለልጄም ሚስትን ውሰድለት።’


ሰዎቹም ለትዕማር፥ “ዐማትሽ የበጎቹን ጠጉር ወደሚሸልቱ ሰዎች ዘንድ ወደ ተምና እየሄደ ነው” አሏት። ይህን እንደ ሰማች


በማዖን ምድር በቀርሜሎስ ንብረት ያለው አንድ ባለጸጋ ሰው ነበረ፤ እርሱም አንድ ሺህ ፍየሎችና በቀርሜሎስ የሚሸልታቸው ሦስት ሺህ በጎች ነበሩት።


ከሁለት ዓመት በኋላ አቤሴሎም በኤፍሬም አቅራቢያ ባለችው በበዓለ ሐጾር ከተማ በጎቹን ይሸልት ነበር፤ ከዚያም የንጉሡን ወንዶች ልጆች ሁሉ በዚያ እንዲገኙለት አቤሴሎም ጋበዛቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች