1 ሳሙኤል 18:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል፥ ጌታ ከዳዊት ጋር እንደ ሆነና ልጁ ሜልኮልም እንደወደደችው በተረዳ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል እግዚአብሔር ከዳዊት ጋራ እንደ ሆነና ልጁ ሜልኮልም እንደ ወደደችው በተረዳ ጊዜ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር መሆኑንና ልጁም ሜልኮል እርሱን እንደ ወደደችው አረጋገጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንደ ሆነ አየ፤ እስራኤልም ሁሉ ወደዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንደ ሆነ አየ፥ እስራኤልም ሁሉ ወደዱት። |
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።
ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎቹ ሄደው ሁለት መቶ ፍልስጥኤማውያንን ገደሉ፤ ለንጉሡ ዐማች ይሆን ዘንድ፥ ሸለፈታቸውን አምጥቶ በቁጥራቸው ልክ ለንጉሡ አቀረበ፤ ከዚያም ሳኦል ልጁን ሜልኮልን ለዳዊት ዳረለት።
ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ የተባረክህ ሁን፤ ብዙ ነገር ታደርጋለህ፤ በእርግጥም ይከናወንልሃል” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደሚሄድበት ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ።