እርሱ ግን ተነስቶ እጁ እስኪዝልና ከሰይፉ ጋር እስኪጣበቅ ድረስ ፍልስጥኤማውያንን ወጋ፤ በዚያችም ዕለት ጌታ ታላቅ ድልን አደረገ። ሕዝቡም ከእርሱ በኋላ ምርኮ ለመግፈፍ ብቻ ተመለሰ።
1 ሳሙኤል 17:52 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነሥተው እየፎከሩ ፍልስጥኤማውያንን እስከ ጋት መግቢያና እስከ ዔቅሮን በሮች ድረስ አሳደዷቸው። የፍልስጥኤማውያንም ሬሳ ከሸዓራይም አንሥቶ እስከ ጋትና ከዚያም እስከ ዔቅሮን በሮች ባለው መንገድ ላይ ወደቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነሥተው እየፎከሩ ፍልስጥኤማውያንን እስከ ጋት መግቢያና እስከ አቃሮን በሮች ድረስ አሳደዷቸው። የፍልስጥኤማውያንም ሬሳ ከሽዓራይም አንሥቶ እስከ ጋት ከዚያም እስከ ዔቅሮን በሮች ባለው መንገድ ላይ ወድቆ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እየፎከሩ እነርሱን በመከተል እስከ ጋትና እስከ ዔቅሮን የቅጽር በሮች ድረስ አሳደዱአቸው፤ የፍልስጥኤማውያን ሬሳ እስከ ጋትና እስከ ዔቅሮን ድረስ ወደ ሻዕራይም በሚያደርሰው መንገድ ሁሉ ወደቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎችም ተነሥተው እልል አሉ፤ ፍልስጥኤማውያንንም እስከ ጌትና እስከ አስቀሎና በር ድረስ አሳደዱአቸው። የፍልስጥኤማውያንም በድኖቻቸው እስከ ጌትና እስከ አቃሮን በሮች ድረስ በመንገድ ላይ ወደቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነሥተው እልል አሉ፥ ፍልስጥኤማውያንንም እስከ ጌትና እስከ አስቀሎና በር ድረስ አሳደዱአቸው። ፍልስጥኤማውያንም ከሸዓራይም ጀምሮ እስከ ጌትና እስከ አቃሮን ድረስ በመንገድ ላይ የተመቱት ወደቁ። |
እርሱ ግን ተነስቶ እጁ እስኪዝልና ከሰይፉ ጋር እስኪጣበቅ ድረስ ፍልስጥኤማውያንን ወጋ፤ በዚያችም ዕለት ጌታ ታላቅ ድልን አደረገ። ሕዝቡም ከእርሱ በኋላ ምርኮ ለመግፈፍ ብቻ ተመለሰ።
ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፤ ወደ ሽክሮን ታጠፈ፤ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤልም በኩል ወጣ፤ የድንበሩም መጨረሻ በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
ስለዚህ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ዔቅሮን ሰደዱት። የእግዚአብሔር ታቦት ዔቅሮን በገባ ጊዜም፥ የዔቅሮን ሕዝብ፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ያመጡብን እኛንና ሕዝባችንን ለማስፈጀት ነው” በማለት ጮኹ።
ከዚህ በኋላ የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች በሙሉ ጠርተው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ምን እናድርገው?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደ ጋት ውሰዱት” አሏቸው። ስለዚህ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወሰዱት።