1 ሳሙኤል 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ከዚህ በኋላ የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች በሙሉ ጠርተው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ምን እናድርገው?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደ ጋት ውሰዱት” አሏቸው። ስለዚህ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወሰዱት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ከዚህ በኋላ የፍልስጥኤማውያንን ገዦች በሙሉ ጠርተው፣ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ምን እናድርገው?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም፣ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደ ጋት ውሰዱት” አሏቸው። ስለዚህ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወሰዱት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 በዚህም ምክንያት ወደ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን ነገሥታት መልእክተኞች ልከው በማስጠራት “ስለ እስራኤል አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት ምን እናድርግ” ብለው ጠየቁአቸው። እነርሱም “ወደ ጋት ውሰዱት” ብለው መለሱላቸው፤ ስለዚህም ጋት ተብላ ወደምትጠራው ወደ ሌላይቱ የፍልስጥኤማውያን ከተማ ወሰዱት፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ወደ እነርሱ ሰበሰቡና፥ “በእስራኤል አምላክ ታቦት ምን እናድርግ?” አሉ፤ የጌት ሰዎችም፥ “የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ እኛ ትዙር” ብለው መለሱ። የእስራኤል አምላክ ታቦትም ወደ ጌት ሄደች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ወደ እነርሱ ሰበሰቡና፦ በእስራኤል አምላክ ታቦት ምን እናድርግ? አሉ፥ እነርሱም፦ የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ ጌት ይዙር ብለው መለሱ። የእስራኤልንም አምላክ ታቦት ወደዚያ ተሸከሙት። ምዕራፉን ተመልከት |