የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 17:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሦስቱ የእሴይ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነት ሄደው ነበር፤ እነርሱም ታላቁ ኤሊአብ፥ ሁለተኛው አሚናዳብ፥ ሦስተኛውም ሻማ ይባላሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሦስቱ የእሴይ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነት ሄደው ነበር፤ እነርሱም ታላቁ ኤልያብ፣ ሁለተኛው አሚናዳብ፣ ሦስተኛውም ሣማ ይባላሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሦስቱ ታላላቅ ልጆቹም ከሳኦል ጋር ወደ ጦርነት ዘምተው ነበር፤ እነርሱም በኲሩ ኤሊአብ፥ ሁለተኛው አሚናዳብ፥ ሦስተኛውም ሻማ ተብለው ይጠሩ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ሴ​ይም ሦስቱ ታላ​ላ​ቆች ልጆቹ ሳኦ​ልን ተከ​ት​ለው ወደ ሰልፉ ሄደው ነበር፤ ወደ ሰል​ፉም የሄ​ዱት የሦ​ስቱ ልጆች ስም ይህ ነበረ፤ ታላቁ ኤል​ያብ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም አሚ​ና​ዳብ፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ሣማዕ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእሴይም ሦስቱ ታላላቆች ልጆቹ ሳኦልን ተከትለው ወደ ሰልፉ ሄደው ነበር፥ ወደ ሰልፉም የሄዱት የሦስቱ ልጆቹ ስም ይህ ነበረ፥ ታላቁ ኤልያብ ሁለተኛውም አሚናዳብ ሦስተኛውም ሣማ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 17:13
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን አምኖን በጣም ዘዴኛ የሆነ፥ ዮናዳብ ተብሎ የሚጠራ ወዳጅ ነበረው፤ እርሱም የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ነበር፤


የዳዊት ወንድም የሻምዓ ልጅ ዮናዳብ ግን እንዲህ አለ፤ “የተገደሉት የንጉሡ ልጆች በሙሉ እንደ ሆኑ አድርጎ ጌታዬ አያስብ፤ የሞተው አምኖን ብቻ ነው። አምኖን እኅቱን ትዕማርን በግድ ከደፈራት ጊዜ አንሥቶ አቤሴሎም ይህን ጉዳይ ቆርጦ የተነሣበት ነበር።


ይህም ሰው እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ፥ የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ዮናታን ገደለው።


እሴይም የወለደው የበኩር ልጁን ኤልያብን፥ ሁለተኛውንም አሚናዳብን፥ ሦስተኛውንም ሳምዓ፥


ታላቅ ወንድሙ ኤሊአብ፥ ዳዊት ከሰዎች ጋር ሲነጋገር በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ፥ “ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂት በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውካቸው? ዕብሪትህንና የልብህን ክፋት ዐውቃለሁ፤ የመጣኸው ጦርነቱን ለማየት ብቻ ነው” አለው።