Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 17:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ሴ​ይም ሦስቱ ታላ​ላ​ቆች ልጆቹ ሳኦ​ልን ተከ​ት​ለው ወደ ሰልፉ ሄደው ነበር፤ ወደ ሰል​ፉም የሄ​ዱት የሦ​ስቱ ልጆች ስም ይህ ነበረ፤ ታላቁ ኤል​ያብ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም አሚ​ና​ዳብ፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ሣማዕ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሦስቱ የእሴይ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነት ሄደው ነበር፤ እነርሱም ታላቁ ኤልያብ፣ ሁለተኛው አሚናዳብ፣ ሦስተኛውም ሣማ ይባላሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሦስቱ የእሴይ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነት ሄደው ነበር፤ እነርሱም ታላቁ ኤሊአብ፥ ሁለተኛው አሚናዳብ፥ ሦስተኛውም ሻማ ይባላሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሦስቱ ታላላቅ ልጆቹም ከሳኦል ጋር ወደ ጦርነት ዘምተው ነበር፤ እነርሱም በኲሩ ኤሊአብ፥ ሁለተኛው አሚናዳብ፥ ሦስተኛውም ሻማ ተብለው ይጠሩ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የእሴይም ሦስቱ ታላላቆች ልጆቹ ሳኦልን ተከትለው ወደ ሰልፉ ሄደው ነበር፥ ወደ ሰልፉም የሄዱት የሦስቱ ልጆቹ ስም ይህ ነበረ፥ ታላቁ ኤልያብ ሁለተኛውም አሚናዳብ ሦስተኛውም ሣማ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 17:13
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለአ​ም​ኖ​ንም የዳ​ዊት ወን​ድም የሳ​ምዓ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ የሚ​ባል ወዳጅ ነበ​ረው፤ ኢዮ​ና​ዳ​ብም እጅግ ብልህ ሰው ነበረ።


የዳ​ዊ​ትም ወን​ድም የሳ​ምዓ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “ጌታዬ ጐል​ማ​ሶቹ የን​ጉሡ ልጆች ሁሉ እንደ ሞቱ አያ​ስብ፤ እኅ​ቱን ትዕ​ማ​ርን በግድ ካስ​ነ​ወ​ራት ጀምሮ በአ​ቤ​ሴ​ሎም ዘንድ የተ​ቈ​ረጠ ነገር ነበ​ረና የሞተ አም​ኖን ብቻ ነው።


እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በተ​ገ​ዳ​ደረ ጊዜ የዳ​ዊት ወን​ድም የሴ​ማይ ልጅ ዮና​ታን ገደ​ለው።


እሴ​ይም የበ​ኵር ልጁን ኤል​ያ​ብን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም አሚ​ና​ዳ​ብን፥ ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም ሣማን፥


ታላቅ ወን​ድ​ሙም ኤል​ያብ ከሰ​ዎች ጋር ሲነ​ጋ​ገር ሰማ፤ ኤል​ያ​ብም በዳ​ዊት ላይ እጅግ ተቈጣ፥ “ለምን ወደ​ዚህ ወረ​ድህ? እነ​ዚ​ያ​ንስ ጥቂ​ቶች በጎች በም​ድረ በዳ ለማን ተው​ሃ​ቸው? እኔ ኵራ​ት​ህ​ንና የል​ብ​ህን ክፋት አው​ቃ​ለ​ሁና ሰል​ፉን ለማ​የት መጥ​ተ​ሃል” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች