1 ሳሙኤል 16:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እዚያ በደረሱ ጊዜም፥ ሳሙኤል ኤልያብን አይቶ፥ “በእርግጥ ጌታ የቀባው ሰው እነሆ፤ በጌታ ፊት ቆሞአል” ብሎ አሰበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እዚያ በደረሱ ጊዜም፣ ሳሙኤል ኤልያብን አይቶ፣ “በርግጥ እግዚአብሔር የቀባው ሰው እነሆ፤ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል” ብሎ ዐሰበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም በደረሱ ጊዜ ሳሙኤል ኤሊአብ ተብሎ የሚጠራውን የእሴይን ልጅ አይቶ “በእግዚአብሔር ፊት የቆመው ይህ ሰው በእርግጥ ለንጉሥነት የተመረጠ ነው” ሲል አሰበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ በመጡ ጊዜ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ፥ “በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ በመጡ ጊዜ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ፦ በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው አለ። |
ነገር ግን የእስራኤል አምላክ ጌታ በእስራኤል ላይ የዘለዓለም ንጉሥ እንድሆን ከአባቴ ቤት ሁሉ መርጦኛል፤ ይሁዳንም አለቃ እንዲሆን መርጦታል፤ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት መርጦአል፤ ከአባቴም ልጆች መካከል በእስራኤል ሁሉ ላይ ሊያነግሠኝና ሊመርጠኝ ወደደ።
ዜባሕና ጻልሙናንም፥ “በታቦር ላይ የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?” በማለት ጠየቃቸው። እነርሱም፥ “ሁሉም እንዲህ እንዳንተ ያሉ የንጉሥ ልጆች የሚመስሉ ናቸው” አሉት።
ሦስቱ የእሴይ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነት ሄደው ነበር፤ እነርሱም ታላቁ ኤሊአብ፥ ሁለተኛው አሚናዳብ፥ ሦስተኛውም ሻማ ይባላሉ፤