1 ሳሙኤል 16:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እንዲህም ሆነ፤ በመጡ ጊዜ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ፥ “በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው” አለ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 እዚያ በደረሱ ጊዜም፣ ሳሙኤል ኤልያብን አይቶ፣ “በርግጥ እግዚአብሔር የቀባው ሰው እነሆ፤ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል” ብሎ ዐሰበ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 እዚያ በደረሱ ጊዜም፥ ሳሙኤል ኤልያብን አይቶ፥ “በእርግጥ ጌታ የቀባው ሰው እነሆ፤ በጌታ ፊት ቆሞአል” ብሎ አሰበ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እዚያም በደረሱ ጊዜ ሳሙኤል ኤሊአብ ተብሎ የሚጠራውን የእሴይን ልጅ አይቶ “በእግዚአብሔር ፊት የቆመው ይህ ሰው በእርግጥ ለንጉሥነት የተመረጠ ነው” ሲል አሰበ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እንዲህም ሆነ፥ በመጡ ጊዜ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ፦ በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው አለ። ምዕራፉን ተመልከት |