1 ሳሙኤል 10:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንተም ጉዞህን በመቀጠል በታቦር እስካለው ባሉጥ ዛፍ ድረስ ትሄዳለህ፤ እዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ግልገል፥ ሌላው ሦስት ዳቦ፥ ሌላው ደግሞ የወይን ጠጅ የተሞላበት አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንተም ጕዞህን በመቀጠል በታቦር እስካለው እስከ ትልቁ ዛፍ ድረስ ትሄዳለህ፤ እዚያም ሦስት ሰዎች፣ አንዱ ሦስት የፍየል ግልገል፣ ሌላው ሦስት ዳቦ፣ ሌላው ደግሞ የወይን ጠጅ የተሞላበት አቍማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም አልፈህ በታቦር ወደሚገኘው ወደ አንድ ትልቅ ዛፍ ትደርሳለህ፤ እዚያም ወደ ቤትኤል ወደ እግዚአብሔር የሚሄዱ ሦስት ሰዎችን ታገኛለህ፤ ከእነርሱ አንዱ ሦስት የፍየል ጠቦቶችን እየሳበ የሚሄድ ሲሆን ሁለተኛው ሰው ሦስት ኅብስት የተሸከመ ነው፤ ሦስተኛውም የወይን ጠጅ የተሞላበት አቁማዳ የተሸከመ ይሆናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ደግሞ አልፈህ፥ ወደ ትልቁ የታቦር ዛፍ ትደርሳለህ፤ በዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ጠቦቶች ሲነዳ፥ ሁለተኛው ሦስት የዳቦ ስልቻ፥ ሦስተኛውም የወይን ጠጅ አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ታገኛለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ደግሞ ወደ ፊት ትሄዳለህ፥ ወደ ታቦር ወደ ትልቁ ዛፍ ትደርሳለህ፥ በዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ጠቦቶች፥ ሁለተኛው ሦስት ዳቦ፥ ሦስተኛውም የወይን ጠጅ አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል፥ |
እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፦ “ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፥ በዚያም ኑር፥ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ ለእግዚአብሔርም መሠውያውን ሥራ።”
ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፥ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን እሠራለሁ።”
እንደ ጌታም ቃል የአጐቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወዳለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ፦ ‘በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን፥ እባክህ፥ ግዛ፤ የርስቱና የመቤዠቱ መብት የአንተ ነውና፤ ለአንተ ግዛው’ አለኝ። ይህም የጌታ ቃል እንደሆነ አወቅሁ።
የእህልም ቁርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ይሁን፤ ለመጠጥም ቁርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የሆነ የወይን ጠጅ ይቅረብ።
እስራኤላውያን ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርንም “ብንያማውያንን ለመውጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” ሲሉ ጠየቁ። ጌታም፥ “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ” ብሎ መለሰ።
እስራኤላውያን ወጥተው እስኪመሽ ድረስ በጌታ ፊት አለቀሱ፤ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመውጋት እንደገና እንውጣን?” ብለው ጌታን ጠየቁ። ጌታም፥ “አዎን፤ ውጡና ውጉቸው” ብሎ መለሰላቸው።
ዲቦራ በንፍታሌም ውስጥ ቃዴስ በተባለች ከተማ ይኖር የነበረውን የአቢኒኤምን ልጅ ባራቅን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ሲል ያዝሃል፤ ‘ተነሣ፤ ከንፍታሌምና ከዛብሎን ዐሥር ሺህ ሰዎች ይዘህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤
ዜባሕና ጻልሙናንም፥ “በታቦር ላይ የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?” በማለት ጠየቃቸው። እነርሱም፥ “ሁሉም እንዲህ እንዳንተ ያሉ የንጉሥ ልጆች የሚመስሉ ናቸው” አሉት።