Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 89:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሰማያት የአንተ ናቸው፥ ምድርም የአንተ ናት፥ ዓለምንና ሞላውንም አንተ መሠረትህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሰሜንንና ደቡብን የፈጠርህ አንተ ነህ፤ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ሐሤት ያደርጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አንተ ሰሜንና ደቡብን ፈጠርክ፤ የታቦርና የሔርሞን ተራራዎች ለአንተ በደስታ ይዘምራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ጥበ​ብን በልብ ለተ​ማሩ፥ ቀኝ​ህን እን​ዲህ ግለጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 89:12
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥ ምድሪቱንም ያለአንዳች ድጋፍ ያንጠለጥላል።


ድንበሩም ወደ ታቦርና ወደ ሻሕጹማ፥ ወደ ቤት-ሳሚስ ደረሰ፥ የድንበራቸውም መጨረሻ ዮርዳኖስ ነበረ፤ ዐሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።


የእስራኤልም ልጆች ያሸነፉአቸው፥ ከአርኖንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ ያለውን ዓረባ ሁሉ በዮርዳኖስም ማዶ በፀሐይ መውጫ ያለውን አገራቸውን የወረሱአቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤


በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፥ በዚያ ጌታ በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘለዓለም አዝዞአልና።


ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፥ ተራሮችም በደስታ ይዘምሩ፥ በምድር ሊፈርድ ይመጣልና።


የአቢኒዔም ልጅ ባራቅ ወደ ታቦር ተራራ መሄዱን ሲሣራ በሰማ ጊዜ፥


ዲቦራ በንፍታሌም ውስጥ ቃዴስ በተባለች ከተማ ይኖር የነበረውን የአቢኒኤምን ልጅ ባራቅን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ሲል ያዝሃል፤ ‘ተነሣ፤ ከንፍታሌምና ከዛብሎን ዐሥር ሺህ ሰዎች ይዘህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤


እኔ ሕያው በመሆኔ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የተባለው ንጉሥ፥ በተራሮች መካከል እንዳለ እንደ ታቦር፥ በባሕርም አጠገብ እንዳለ እንደ ቀርሜሎስ፥ እንዲሁ በእውነት ይመጣል።


ጌታ ሕዝቡን አጽናንቶአልና፥ ለችግረኞቹም ራርቶአልና ሰማያት ሆይ፥ ዘምሩ፥ ምድር ሆይ፥ ደስ ይበልሽ ተራሮችም ሆይ፥ እልል በሉ።


የዳዊት መዝሙር። ምድርና ሞላዋ የጌታ ናቸው፥ ዓለምና በእርሷም የሚኖሩ ሁሉ።


እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቶአታልና፥ በፈሳሾችም ላይ አጽንቶአታልና።


ሰማያት የጌታ ሰማያት ናቸው፥ ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች