1 ሳሙኤል 10:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ የሳኦል አጎት እርሱንና አገልጋዩን፥ “የት ነበራችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እርሱም፥ “አህዮቹን ፍለጋ ሄደን ነበር፤ እንደማይገኙ በተረዳን ጊዜ ግን ወደ ሳሙኤል ሄድን” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የሳኦል አጎት እርሱንና አገልጋዩን፣ “የት ነበራችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እርሱም፣ “አህዮቹን ፍለጋ ሄደን ነበር፤ እንደማይገኙ በተረዳን ጊዜ ግን ወደ ሳሙኤል ሄድን” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳኦል አጐት ሳኦልንና አገልጋዩን አይቶ “የት ነበራችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። ሳኦልም “አህዮች ልንፈልግ ሄደን ልናገኛቸው ስላልቻልን ሳሙኤልን ለመጠየቅ ጎራ ብለን ነበር” ሲል መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቤተ ሰቡም አንዱ እርሱንና ብላቴናውን፥ “ወዴት ሄዳችሁ ኖሮአል?” አላቸው። እነርሱም፥ “አህዮችን ልንፈልግ ሄደን ነበር፤ ባጣናቸውም ጊዜ ወደ ሳሙኤል መጣን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አጎቱም ሳኦልንና ብላቴናውን፦ ወዴት ሄዳችሁ ኖርአል? አላቸው። እርሱም፦ አህዮችን ልንሻ ሄደን ነበር፥ ባጣናቸውም ጊዜ ወደ ሳሙኤል መጣን አለ። |