1 ሳሙኤል 10:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው፥ “አባታቸውስ ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለዚህ፥ “ሳኦልም ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌያዊ አነጋገር ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው፣ “የእነርሱስ አባት ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለዚህ፣ “ሳኦልም ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌያዊ አነጋገር ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም የሚኖር አንድ ሰው “የእነዚህስ የሌሎቹ ነቢያት ሁኔታ እንዴት ነው? አባቶቻቸውስ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀ፤ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል የምሳሌ አነጋገር የመነጨውም ከዚህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ስፍራ ያለ አንድ ሰው፥ “አባቱስ ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለዚህም “ሳኦል ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ስፍራ ያለ አንድ ሰው፦ አባታቸውስ ማን ነው? ብሎ መለሰ። ስለዚህም፦ ሳኦል ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን? የሚል ምሳሌ ሆነ። |
ስለዚህ ሳኦል በራማ ወደምትገኘው ወደ የራማዋ ናዮት ሄደ፤ ሲሄድ ሳለም የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ ደግሞ ወረደ፤ ወደ ናዮት እስኪደርስ ድረስም ትንቢት እየተናገረ ተጓዘ።
እርሱም ልብሱን አውልቆ፥ በሳሙኤልም ፊት ደግሞ ትንቢት ተናገረ፤ በዚህ ሁኔታም ቀኑንና ሌሊቱን በሙሉ ራቁቱን ተጋደመ። ሕዝቡ፥ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቆጠረ?” ካለው የተነሣ ነው።