1 ሳሙኤል 19:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ስለዚህ ሳኦል በራማ ወደምትገኘው ወደ የራማዋ ናዮት ሄደ፤ ሲሄድ ሳለም የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ ደግሞ ወረደ፤ ወደ ናዮት እስኪደርስ ድረስም ትንቢት እየተናገረ ተጓዘ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ስለዚህ ሳኦል በአርማቴም ወደምትገኘው ወደ ነዋት ዘራማ ሄደ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በርሱም ላይ ደግሞ ወረደ፤ ወደ ነዋት እስኪደርስ ድረስም ትንቢት እየተናገረ ተጓዘ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ወደዚያም በማምራት ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ ወረደበት፤ እስከ ናዮት በሚያደርሰው መንገድ ሁሉ ትንቢት ይናገር ነበር፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ወደ አውቴዘራማም ሄደ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ደግሞ ወረደ፤ እርሱም ሄደ፤ ወደ አውቴዘራማም እስኪመጣ ድረስ ትንቢት ይናገር ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ወደ አርማቴምም አገር ወደ ነዋትዘራማ ሄደ፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ደግሞ ወረደ፥ እርሱም ሄደ፥ ወደ አርማቴምም አገር ወደ ነዋትዘራማ እስኪመጣ ድረስ ትንቢት ይናገር ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |