ከእነዚህ ነገሮች በኋላ ኒቃኖር ወደ ጽዮን ተራራ ወጣ፤ ካህናት በሰላም እጅ ለመንሳትና ስለ ንጉሡ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕትን ለእርሱ ለማሳየት ከሕዝብ ሽማግሌዎች ጋር ሆነው ከቤተ መቅደስ ወጡ።