ሰዎቹ ጦርነት ሊገጥማቸው የሚመጣውን የጦር ሠራዊት ባዩ ጊዜ ይሁዳን፥ “እኛ በቍጥር ጥቂቶች ነን፤ ታዲያ ከኛ በጣም ከሚበዙት ሰዎች ጋር መዋጋት እንዴት እንችላለን? ዛሬ ምንም ሳንበላ ነው የዋልነው ደክሞናል” አሉት።