በዚያን ጊዜ ከእስራኤል ውስጥ ሕግ አፈራሾች ወጡና ብዙ ሰዎችን አሳሳቱ፥ “ኑ እንሂድና በዙሪያችን ካሉት አሕዛብ ጋር እንስማማ፤ ምክንያቱም ብዙ ክፉ ነገሮች የመጣብን ከእነርሱ በመለየታችን ነው” አሉ።