ባርያዎቹም፦ “ንጉስ ሆይ! ከአንተ ጋር ሆና የምትንከባከብህ ወጣት ልጃገረድ ፈልገን እናምጣ፤ በጌታችንም በንጉሡ እቅፍ ተኝታ ታሞቅሃለች” አሉት።
1 ነገሥት 1:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሁሉም የእስራኤል ግዛት የተዋበች ቆንጆ ፈለጉ፤ አቢሻግንም ሹኔም ከምትባል ስፍራ አገኙ፤ ወደ ንጉሡም ይዘዋት መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በመላው እስራኤል ቈንጆ ልጃገረድ ፈልገው ሱነማዪቱን አቢሳን አገኙ፤ ለንጉሡም አመጡለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዲት ቈንጆ ልጃገረድ ለማግኘት በመላው እስራኤል ፍለጋ ተደረገ፤ ሹኔም ተብላ ከምትጠራው ስፍራ አቢሻግ የምትባል አንዲት ልጃገረድ አግኝተው ለንጉሡ አመጡለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤልም ሀገር ሁሉ የተዋበች ቆንጆ ፈለጉ፤ ሱነማዪቱን አቢሳንም አገኙ፤ ወደ ንጉሡም ወሰዱአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤልም አገር ሁሉ የተዋበች ቆንጆ ፈለጉ፤ ሱነማይቱን አቢሳንም አገኙ፤ ወደ ንጉሡም ይዘዋት መጡ። |
ባርያዎቹም፦ “ንጉስ ሆይ! ከአንተ ጋር ሆና የምትንከባከብህ ወጣት ልጃገረድ ፈልገን እናምጣ፤ በጌታችንም በንጉሡ እቅፍ ተኝታ ታሞቅሃለች” አሉት።
እርሷም ከዚያ ተነሥታ ኤልሳዕ ወደ ነበረበት ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣች። ኤልሳዕም ገና በሩቅ ሳለች ወደ እርሱ ስትመጣ አይቶ አገልጋዩን ግያዝን “ተመልከት! ያቺ ሴት ከሱነም ወደዚህ በመምጣት ላይ ናት!
አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርሷም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤