Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 4:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርሷም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደ ሱነም ሄደ። በዚያም አንዲት ሀብታም ሴት ነበረች፤ እርሷም ምግብ እንዲበላ አጥብቃ ለመነችው፤ በዚያም ባለፈ ቍጥር ምግብ ለመብላት ወደ ቤቷ ይገባ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርስዋም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከዚ​ህም በኋላ አንድ ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ኤል​ሳዕ ወደ ሱማን አለፈ፤ በዚ​ያም ታላቅ ሴት ነበ​ረች፤ እን​ጀ​ራም ይበላ ዘንድ አቆ​መ​ችው፤ በዚ​ያም ባለፈ ቍጥር እን​ጀራ ሊበላ ወደ​ዚያ ይገባ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አንድ ቀንም እንዲህ ሆነ፤ ኤልሳዕ ወደ ሱነም አለፈ፤ በዚያም ታላቅ ሴት ነበረች፤ እንጀራ ይበላ ዘንድ የግድ አለችው፤ በዚያም ባለፈ ቍጥር እንጀራ ሊበላ ወደዚያ ይገባ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 4:8
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ድንበራቸውም የሚያጠቃልለው ኢይዝራኤልን፥ ከስሎትን፥ ሱነምን፥


እነርሱ ግን “እኛ ጋር እደር፤ እየመሸ ነው፥ ቀኑም እያለቀ ነውና፤” ሲሉ አጥብቀው ለመኑት፤ እርሱም እነርሱ ጋር ሊያድር ገባ።


በዕድሜ ያረጁ የግድ ጠቢባን አይደሉም፥ ሽማግሌዎችም የግድ ፍርድን አያስተውሉም።


ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች፥ አምስት መቶ እንስት አህዮችና እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ።


እጅግም ዘበዘባቸው፥ ወደ እርሱም አቀኑ፥ ወደ ቤቱም ገቡ፥ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ እነርሱም በሉ።


በሁሉም የእስራኤል ግዛት የተዋበች ቆንጆ ፈለጉ፤ አቢሻግንም ሹኔም ከምትባል ስፍራ አገኙ፤ ወደ ንጉሡም ይዘዋት መጡ።


እንዲሁም ገለዓዳዊው ባርዚላይ ከሮገሊም ወረደ፤ ንጉሡን ለመሸኘትም አብሮት ዮርዳኖስን ተሻገረ።


ሽማግሌውም፥ “ኑ ግቡ በቤቴም እደሩ፤ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አቀርባለሁ፤ በዐደ ባባይ ግን አትደሩ” አለው።


እርሷም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ “በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ፤” ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።


በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅም ሆነ የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል፤


በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፥ በከንፈርዋ ልዝብነት ትጐትተዋለች።


ሕፃኑም አደገ፤ በመከር ወራት አንድ ቀን ጧት ያ ልጅ ከአጫጆች ጋር በእርሻ ውስጥ ወደነበረው ወደ አባቱ ሄደ፤


ፍልስጥኤማውያን ተሰብስበው በመምጣት በሹኔም ሲሰፍሩ፥ ሳኦል ደግሞ እስራኤላውያንን ሁሉ ሰብስቦ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ሰፈረ።


ጌታውም አገልጋዩን ‘ቤቴ እንዲሞላ ወደ ጎዳናዎችና ወደ ገጠር መንገዶች ውጣና እንዲገቡ ገፋፋቸው፤


እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች