1 ነገሥት 1:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤርሳቤህም አጎንብሳ ለንጉሡ እጅ ነሣች፥ ንጉሡም፦ “ምን ትፈልጊያለሽ?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤርሳቤህም ለጥ ብላ እጅ ከነሣች በኋላ እፊቱ በጕልበቷ ተንበረከከች። ንጉሡም፣ “ምን ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤርሳቤህም ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ ነሣች፤ ንጉሡም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤርሳቤህም አጎንብሳ ለንጉሡ ሰገደች፤ ንጉሡም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤርሳቤህም አጎንብሳ ለንጉሡ እጅ ነሣች፤ ንጉሡም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አለ። |
እርሷም አለችው፦ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ለባርያህ፦ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፥ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ በጌታ በእግዚአብሔር ምለህልኛል፥
ለንጉሡም፦ “እነሆ፥ ነቢዩ ናታን መጥቷል” ብለው ነገሩት፥ እርሱም ወደ ንጉሡ ፊት በገባ ጊዜ በግምባሩ በምድር ላይ ተደፍቶ ለንጉሡ እጅ ነሣ።
እርሷም “እንድትፈጽምልኝ የምጠይቅህ አንድ ትንሽ ጉዳይ አለኝ፤ እባክህ እምቢ በማለት አታሳፍረኝ” አለችው። ንጉሡም “እናቴ ሆይ! አላሳፍርሽም፤ ጉዳዩ ምንድነው” አላት።
ልጁ ከሄደ በኋላ፥ ዳዊት ከድንጋዩ በስተ ደቡብ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ በዮናታን ፊት ሦስት ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደለት፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱም፤ በይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር።