የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ቆሮንቶስ 16:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፍቅሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፍቅሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ከሁላችሁ ጋራ ነው። አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፍቅሬ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ኔም ፍቅር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን። አሜን። በኤ​ፌ​ሶን ተጽፎ በጢ​ሞ​ቴ​ዎ​ስና በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ፥ በፈ​ር​ዶ​ና​ጥ​ስና በአ​ካ​ይ​ቆስ እጅ ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች የተ​ላ​ከው መጀ​መ​ሪ​ያዉ መል​እ​ክት ተፈ​ጸመ። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፍቅሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ከሁላችሁ ጋር ነው። አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ቆሮንቶስ 16:24
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው፤ እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።’


እንዲህማ ካልሆነ፥ በመንፈስ በምትባርክበት ጊዜ፥ አንተ የምትለውን የማያውቅ እንግዳ ሰው ካልተረዳ፥ እንዴት አድርጎ ለምስጋናህ፥ “አሜን” ሊል ይችላል?


የምታደርጉትን ሁሉ በፍቅር አድርጉ።


የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።


በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ ከወንድማችንም ከጢሞቴዎስ፥ በመላው አካይያ ከሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ ጋር በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፤


ስለምን? ስለማልወዳችሁ ይመስላችኋል? እንደምወዳችሁ እግዚአብሔር ያውቃል።


እኔ ግን ስለ ነፍሳችሁ በብዙ ደስታ ገንዘቤን አወጣለሁ፤ ራሴን እንኳ እከፍላለሁ። ከመጠን ይልቅ ብወዳችሁ፥ የናንተ ፍቅር እንዴት ያንሳል?


በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ሁላችሁንም ምን ያኽል እንደምናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ተነሣሣ፤ ንስሓም ግባ።