ለረኃባቸው ከሰማይ ምግብ ሰጠሃቸው፥ ለጥማታቸውም ከዓለቱ ውኃ አፈለቅህላቸው፤ ልትሰጣቸው ወደ ማልክላቸው ምድር ገብተው እንዲወርሱ ነገርካቸው።”
1 ቆሮንቶስ 10:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ ምግብ በሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም ከአንድ መንፈሳዊ ምግብ በሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉም አንድ ዐይነት መንፈሳዊ ምግብ ተመገቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም ያን መንፈሳዊ ምግብ ተመገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ |
ለረኃባቸው ከሰማይ ምግብ ሰጠሃቸው፥ ለጥማታቸውም ከዓለቱ ውኃ አፈለቅህላቸው፤ ልትሰጣቸው ወደ ማልክላቸው ምድር ገብተው እንዲወርሱ ነገርካቸው።”
የእስራኤልም ልጆች ባዩት ጊዜ ያ ምን እንደሆነ አላወቁምና ሁሉም ሰው ወንድሙን፦ “ይህ ምንድነው?” በማለት ተጠያየቁ። ሙሴም፦ “እንድትበሉት ጌታ የሰጣችሁ ምግብ ነው።”
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ ከሰማይ እንጀራን ላዘንብላችሁ ነው፤ ሕዝቡም ወጥተው ለቀኑ የሚበቃቸውን በቀኑ ይልቀሙ በሕጌ ይሄዱ ወይም አይሄዱ እንደሆነ እፈትናቸዋለሁ።
ሰው የሚኖረው በእንጀራ ብቻ ሳይሆን ከጌታ አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር ሊያሳውቅህ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥ አንተም ያላወቅኸውን፥ አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።