Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 9:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እንዲያስተምራቸው መልካሟን መንፈስህን ሰጠሃቸው፥ መናህን ከአፋቸው አልከለከልክም፥ ለጥማታቸውም ውኃን ሰጠሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ያስተምራቸው ዘንድ ቸር መንፈስህን ሰጠሃቸው፤ መናውን ከአፋቸው አልከለከልህም፤ በተጠሙ ጊዜ ውሃ ሰጠሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 የሚያስተምራቸውን ቸር መንፈስህን ሰጠሃቸው፤ የሚመገቡትን መና፥ የሚጠጡትንም ውሃ ሰጠሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ያስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ውም ዘንድ መል​ካ​ሙን መን​ፈ​ስ​ህን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ መና​ህ​ንም ከአ​ፋ​ቸው አል​ከ​ለ​ከ​ል​ህም፤ ለጥ​ማ​ታ​ቸ​ውም ውኃን ሰጠ​ሃ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ያስተምራቸውም ዘንድ መልካሙን መንፈስህን ሰጠሃቸው፥ መናህንም ከአፋቸው አልከለከልህም፥ ለጥማታቸውም ውኃ ሰጠሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 9:20
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፥ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።


እኔም እወርዳለሁ፥ በዚያም ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ፥ በአንተ ካለውም መንፈስ ወስጄ በእነርሱ ላይ አኖረዋለሁ፤ አንተም ብቻህን እንዳትሸከም የሕዝቡን ሸክም ከአንተ ጋር ይሸከማሉ።


ኢየሱስ መልሶ “የእግዚአብሔርን ስጦታና ‘ወሃ አጠጪኝ’ የሚልሽ ማን መሆኑን ብታውቂ ኖሮ፥ አንቺ በለመንሽው ነበር፤ የሕይወትም ውሃ በሰጠሽ ነበር፤” አላት።


ማንኛውም ትንቢት በሰው ፈቃድ ከቶ አልመጣም፤ ነገር ግን ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ የተመሩ ሰዎች ከእግዚአብሔር ተቀብለው ተናገሩ።


በምድረ በዳ በኩል በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም፤ ውኃንም ከዓለቱ ውስጥ አፈለቀላቸው፥ ዓለቱንም ሰነጠቀ ውኃውም ፈሰሰ።


የብርሃን ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና፤


እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በእርሱ ውስጥ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እንጂ፤” አላት።


ዓለቱን ሰነጠቀ፥ ውኃውም ፈለቀ፥ ወንዞች በበረሃ ፈሰሱ፥


በማግስቱም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚያም በኋላ ለእስራኤል ልጆች መና አልመጣላቸውም፤ ነገር ግን በዚያው ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።


እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ከእርሱ ውኃ ይወጣል፥ ሕዝቡም ከእርሱ ይጠጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ።


የእስራኤልም ልጆች ባዩት ጊዜ ያ ምን እንደሆነ አላወቁምና ሁሉም ሰው ወንድሙን፦ “ይህ ምንድነው?” በማለት ተጠያየቁ። ሙሴም፦ “እንድትበሉት ጌታ የሰጣችሁ ምግብ ነው።”


ነገር ግን ብዙ ዓመታት ታገሥሃቸው፥ በነቢያትህም እጅ በመንፈስህ መሰከርክባቸው፥ አላደመጡም፥ ስለዚህም በምድር አሕዛብ እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው።


ወንድሞች ሆይ! ስለ እኔ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ከእኔ ጋር እንድትጋደሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ፍቅር እለምናችኋለሁ፤


የሚራራላቸውም ይመራቸዋልና፥ በውኃም ምንጮች በኩል ይነዳቸዋልና አይራቡም፥ አይጠሙም፥ የበረኅ ትኩሳት ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም።


የእስራኤልም ልጆች ወደሚኖሩባት ምድር እስኪመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ፤ ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስኪመጡ ድረስ መና በሉ።


ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ ምግብ በሉ፤


ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ የገባሁላችሁ ቃል ነው መንፈሴ በመካከላችሁ ይቆማልና አትፍሩ።


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ ከሰማይ እንጀራን ላዘንብላችሁ ነው፤ ሕዝቡም ወጥተው ለቀኑ የሚበቃቸውን በቀኑ ይልቀሙ በሕጌ ይሄዱ ወይም አይሄዱ እንደሆነ እፈትናቸዋለሁ።


ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ ሕዝቡም በሙሴ ላይ አጉረመረሙ “እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብጽ አወጣኸን?” አሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች