አንተ አባታችን አዳምን ፈጠርኸው፤ ትረዳውና ታሳርፈውም ዘንድ ሔዋንን ሰጠኸው፤ ከእነዚያም የሰው ዘር ተወለደ፤ አንተም አልህ፦ ‘ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለምና የሚረዳውን እንፍጠርለት።’
አዳምን የፈጠርህ አንተ ነህ፥ ረዳትና አጋዥ እንድትሆነው ሚስቱን ሔዋንን የፈጠርህለት አንተ ነህ፤ የሰው ዘር ሁሉ የተወለደው ከሁለቱ ነው። ‘ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለም፥ እሱን የምትመስል ረዳት እንፈጠርለት’ ያልህ አንተ ነህ።