ዘኍል 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከሌዊ ልጆች መካከል በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች የቀዓትን ልጆች ለዩአቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከሌዋውያን ወገን የቀዓት ዘር የሆኑትን በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው ቍጠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከሌዊ ልጆች መካከል የቀዓትን ልጆች በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች ላይ የሕዝብ ቈጠራ አድርግ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከሌዊ ልጆች መካከል የቀዓትን ዘር በየቤተሰባቸውና በየጐሣቸው ቊጠር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሌዊ ልጆች መካከል በየወገናቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች የቀዓትን ልጆች ድምር ውሰድ፤ |
ለቀዓትም የእንበረም ወገን፥ የይስዓር ወገን፥ የኬብሮንም ወገን፥ የአዛሔልም ወገን ነበሩ፤ የቀዓት ወገኖች እነዚህ ናቸው።
ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በምስክሩ ድንኳን ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡበትን ሁሉ ትለያለህ።