የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 36:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ደ​ዚ​ህም ከአ​ንድ ነገድ ወደ ሌላ ነገድ ምንም ርስት አይ​ተ​ላ​ለፍ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገድ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ርስቱ ይጠጋ።”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ የወረሰውን መሬት እንዳለ ማቈየት ስላለበት፣ ርስት ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ አይተላለፍም።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህም ከአንድ ነገድ ወደ ሌላ ነገድ ምንም ርስት አይተላለፍ ከእስራኤልም ልጆች ነገድ እያንዳንዱ የራሱን ርስት ይያዝ።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ያም ርስት ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ ሊተላለፍ አይቻልም፤ እያንዳንዱ ነገድ የራሱን ርስት እንደ ያዘ ይኖራል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንደዚህም ከአንድ ነገድ ወደ ሌላ ነገድ ምንም ርስት አይተላለፍ ከእስራኤልም ልጆች ነገድ እያንዳንዱ ወደ ርስቱ ይጠጋ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 36:9
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ወልደ አዴር እን​ዲህ ይላል፦ ብር​ህና ወር​ቅህ የእኔ ነው፤ ሚስ​ቶ​ች​ህና ልጆ​ች​ህም የእኔ ናቸው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች አደ​ረጉ።


እን​ደ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት ከነ​ገድ ወደ ነገድ ምንም አይ​ተ​ላ​ለፍ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ አባ​ቶቹ ነገድ ርስት ይጠጋ።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው የአ​ባ​ቶ​ቹን ርስት ይወ​ርስ ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገድ ሁሉ፥ ርስት ያላት ሴት ልጅ ሁሉ ከአ​ባቷ ነገድ ባል ታግባ።


ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን አሰ​ና​በተ፤ ሁሉም ወደ​የ​ቦ​ታ​ቸው ገቡ።


አሁ​ንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእ​ኔን የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ ላይ አስ​ነ​ሥ​ቶህ እን​ደ​ሆነ፥ ቍር​ባ​ን​ህን ይቀ​በል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አም​ልክ ብለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ላይ እን​ዳ​ል​ቀ​መጥ ዛሬ ጥለ​ው​ኛ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርጉ​ማን ይሁኑ።