የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 36:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ደ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት ከነ​ገድ ወደ ነገድ ምንም አይ​ተ​ላ​ለፍ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ አባ​ቶቹ ነገድ ርስት ይጠጋ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እያንዳንዱ እስራኤላዊም ከቀደሙት አባቶቹ በወረሰው ርስት ይጽና፤ በእስራኤል ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ የሚተላለፍ ርስት አይኖርም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህም የእስራኤል ልጆች ርስት ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ አይተላለፍ፤ ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ የአባቶቹን ነገድ ርስት ይያዝ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ዐይነት የማንኛውም እስራኤላዊ ርስት ወደ ሌላ ነገድ አይተላለፍም፤ ከገዛ ነገዱ ጋር የተያያዘ ይሆናል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንደዚህም የእስራኤል ልጆች ርስት ከነገድ ወደ ነገድ ምንም አይተላለፍ፤ ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ ወደ አባቶቹ ነገድ ርስት ይጠጋ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 36:7
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ወልደ አዴር እን​ዲህ ይላል፦ ብር​ህና ወር​ቅህ የእኔ ነው፤ ሚስ​ቶ​ች​ህና ልጆ​ች​ህም የእኔ ናቸው።”


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው የአ​ባ​ቶ​ቹን ርስት ይወ​ርስ ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገድ ሁሉ፥ ርስት ያላት ሴት ልጅ ሁሉ ከአ​ባቷ ነገድ ባል ታግባ።


እን​ደ​ዚ​ህም ከአ​ንድ ነገድ ወደ ሌላ ነገድ ምንም ርስት አይ​ተ​ላ​ለፍ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገድ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ርስቱ ይጠጋ።”


ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን አሰ​ና​በተ፤ ሁሉም ወደ​የ​ቦ​ታ​ቸው ገቡ።


አሁ​ንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእ​ኔን የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ ላይ አስ​ነ​ሥ​ቶህ እን​ደ​ሆነ፥ ቍር​ባ​ን​ህን ይቀ​በል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አም​ልክ ብለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ላይ እን​ዳ​ል​ቀ​መጥ ዛሬ ጥለ​ው​ኛ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርጉ​ማን ይሁኑ።