ሣራም በቈላ ውስጥ ባለች አርባቅ በምትባል ከተማ ሞተች፤ እርስዋም በከነዓን ምድር ያለች ኬብሮን ናት፤ አብርሃምም ለሣራ ሊያዝንላትና ሊያለቅስላት ተነሣ።
ሉቃስ 8:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም እያለቀሱ ዋይ ዋይ ይሉላት ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን፥ “አታልቅሱ፤ ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ እያለቀሱላት ዋይ ዋይ ይሉ ነበር። እርሱ ግን፣ “አታልቅሱ፤ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም እያለቀሱ ደረታቸውን ይመቱላት ነበር። እርሱ ግን፦ “አታልቅሱ፤ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም፤” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ስለ ልጅትዋ ያለቅሱ! ዋይ ዋይም ይሉ ነበር። ኢየሱስ ግን “አታልቅሱ፤ ልጅትዋ አንቀላፍታለች እንጂ አልሞተችም፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉም እያለቀሱላት ዋይ ዋይ ይሉ ነበር። እርሱ ግን፦ አታልቅሱ፤ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም አለ። |
ሣራም በቈላ ውስጥ ባለች አርባቅ በምትባል ከተማ ሞተች፤ እርስዋም በከነዓን ምድር ያለች ኬብሮን ናት፤ አብርሃምም ለሣራ ሊያዝንላትና ሊያለቅስላት ተነሣ።
ንጉሡም እጅግ ደነገጠ፤ በበሩም ላይ ወዳለችው ሰገነት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፥ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ በአንተ ፋንታ እኔ እንድሞት ቤዛህም እንድሆን ማን ባደረገኝ፥ ልጄ አቤሴሎም፥ ልጄ ሆይ፥” ይል ነበር።
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።
ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ከጴጥሮስ፥ ከያዕቆብና ከዮሐንስ፥ ከብላቴናይቱም አባትና እናት በቀር ማንም ከእርሱ ጋር ሌላ ሰው ይገባ ዘንድ አልፈቀደም።
ጌታችን ኢየሱስም ሰምቶ እንዲህ አለ፥ “ይህ ደዌ በእርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም።”