የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሉቃስ 24:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚ​ህም ነገር የሚ​ሉ​ትን አጥ​ተው ሲያ​ደ​ንቁ ሁለት ሰዎች ከፊ​ታ​ቸው ቆመው ታዩ​አ​ቸው፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም ያብ​ረ​ቀ​ርቅ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሁኔታው ግራ ተጋብተው ሳሉ፣ እነሆ፤ እጅግ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች ድንገት አጠገባቸው ቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም በዚህ ሲገረሙ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም ነገር በመገረም ላይ ሳሉ እነሆ፥ የሚያንጸባርቅ ብሩህ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች መጥተው በአጠገባቸው ቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት



ሉቃስ 24:4
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዐይ​ኑ​ንም በአ​ነሣ ጊዜ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያ​ቸ​ውም ጊዜ ሊቀ​በ​ላ​ቸው ከድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ተነ​ሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድ​ርም ሰገደ፤


ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጐናጸፈ ጐልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ።


እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው ቆመ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃን በዙ​ሪ​ያ​ቸው አበራ፤ ታላቅ ፍር​ሀ​ት​ንም ፈሩ።


ፈር​ተ​ውም ፊታ​ቸ​ውን ወደ ምድር አቀ​ረ​ቀሩ። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “ሕያ​ዉን ከሙ​ታን ጋር ለምን ትሹ​ታ​ላ​ችሁ?


እነ​ር​ሱም ወደ ሰማይ አተ​ኵ​ረው ሲመ​ለ​ከቱ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች ነጫጭ ልብስ ለብ​ሰው በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው ቆመው ታዩ​አ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወርዶ በአ​ጠ​ገቡ ቆመ፤ በቤ​ትም ውስጥ ብር​ሃን ሆነ፤ ጴጥ​ሮ​ስ​ንም ጎኑን ነክቶ ቀሰ​ቀ​ሰ​ውና፥ “ፈጥ​ነህ ተነሥ” አለው፥ ሰን​ሰ​ለ​ቶ​ቹም ከእ​ጆቹ ወል​ቀው ወደቁ።


እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።