የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 24:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ተቀ​መ​ጡት ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ምድ​ርም ወሰ​ድ​ኋ​ችሁ፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ተዋጉ፤ ሙሴም ተዋ​ጋ​ቸው፤ አሳ​ል​ፌም በእ​ጃ​ችሁ ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ወረ​ሳ​ችሁ፤ ከፊ​ታ​ች​ሁም አጠ​ፋ​ኋ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘በምሥራቅ ዮርዳኖስ ወደሚኖሩት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፤ እነርሱ ወጓችሁ፤ እኔ ግን አሳልፌ በእጃችሁ ሰጠኋቸው፤ ከፊታችሁ አጠፋኋቸው፤ እናንተም ምድራቸውን ወረሳችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፤ ከእናንተም ጋር ተዋጉ፥ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ፥ ምድራቸውንም ወረሳችሁ፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም በኋላ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ወደሚኖሩት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፤ እነርሱ ተዋጉአችሁ፤ እኔ ግን በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጀኋቸው፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው፤ ምድራቸውንም ወረሳችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፥ ከእናንተም ጋር ተዋጉ፥ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ፥ ምድራቸውንም ወረሳችሁ፥ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 24:8
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንና አሕ​ዛ​ብን ዕድል ፈንታ አድ​ር​ገህ ሰጠ​ሃ​ቸው፤ የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ የሴ​ዎ​ንን ምድር፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ የዐ​ግን ምድር ወረሱ።


መል​አኬ በፊ​ትህ ይሄ​ዳ​ልና፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ያገ​ባ​ሃል፤ እኔም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


የአ​ሞ​ራ​ዊ​ው​ንም ምድር ትወ​ርሱ ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ኋ​ችሁ፤ በም​ድረ በዳም አርባ ዓመት መራ​ኋ​ችሁ።


እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብር​ታ​ቱም እንደ ወይራ ዛፍ የነ​በ​ረ​ውን አሞ​ራ​ዊ​ውን ከፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋሁ፤ ፍሬ​ው​ንም ከላዩ፥ ሥሩ​ንም ከታቹ አጠ​ፋሁ።


ሴዎ​ንም ሕዝ​ቡም ሁሉ ሊዋ​ጉን ወደ ኢያሳ ወጡ።


በሐ​ሴ​ቦ​ንም የነ​ገሠ የአ​ሞ​ሬ​ዎን ንጉሥ የሴ​ዎን ከተ​ሞ​ችን ሁሉ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፥