የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰዎ​ቹም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መሻ​ገ​ሪያ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ በሩም ተቈ​ለፈ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰዎቹም ሰላዮቹን በመከታተል ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ የሚወስደውን መንገድ ይዘው ሄዱ፤ አሳዳጆቹ ወጥተው እንደ ሄዱም የቅጥሩ በር ተዘጋ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰዎቹም ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ እስከሚወስደው መንገድ ድረስ አሳደዱአቸው፤ አሳዳጆችም ከወጡ በኋላ በሩ ተዘጋ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የንጉሡም መልእክተኞች ከከተማይቱ ወጥተው ሄዱ፤ የቅጽር በሩም ተዘጋ፤ መልእክተኞቹም ሰላዮችን በመፈለግ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሮ እስከሚያልፈው ስፍራ ድረስ ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰዎቹም ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ በሚወስደው መንገድ አሳደዱአቸው፥ አሳዳጆችም ከወጡ በኋላ በሩ ተቈለፈ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 2:7
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ወኅኒ ቤቱ​ንም ዙሪ​ያ​ውን ተዘ​ግቶ በቍ​ል​ፍም ተቈ​ልፎ አገ​ኘ​ነው፤ ወታ​ደ​ሮ​ቹም በሩን ይጠ​ብቁ ነበር፤ ነገር ግን ከፍ​ተን በገ​ባን ጊዜ በው​ስጥ ያገ​ኘ​ነው የለም” አሉ​አ​ቸው።


በሩም ሲዘጋ፥ ሲጨ​ል​ምም ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላ​ው​ቅም፤ ፈጥ​ና​ችሁ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ ምን​አ​ል​ባት ታገ​ኙ​አ​ቸው ይሆ​ናል” አለ​ቻ​ቸው።


እር​ስዋ ግን ወደ ሰገ​ነቱ አው​ጥታ በተ​ከ​መረ እን​ጨት መካ​ከል በቀ​ር​ከሃ ጠቅ​ልላ ደብ​ቃ​ቸው ነበር።


እነ​ዚ​ህም ሳይ​ተኙ ሴቲቱ ወደ እነ​ርሱ ወደ ሰገ​ነቱ ወጣች።


የገ​ለ​ዓድ ሰዎ​ችም ኤፍ​ሬም በሚ​ያ​ል​ፍ​በት በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ደረ​ሱ​ባ​ቸው። ከዚህ በኋላ ከኤ​ፍ​ሬም ያመ​ለ​ጡት እን​ሻ​ገር ባሉ ጊዜ የገ​ለ​ዓድ ሰዎች፥ “በውኑ እና​ንተ ከኤ​ፍ​ሬም ወገን ናች​ሁን?” ቢሉ​አ​ቸው “አይ​ደ​ለ​ንም” አሉ።


እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንን ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ና​ልና ተከ​ተ​ሉኝ” አላ​ቸው። ተከ​ት​ለ​ው​ትም ወረዱ፤ ወደ ሞዓ​ብም የሚ​ያ​ሻ​ግ​ረ​ውን የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን መሻ​ገ​ርያ ያዙ፤ ማንም ሰው እን​ዲ​ያ​ልፍ አል​ፈ​ቀ​ዱም።