የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ፥ “እነሆ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሰላ​ዮች ሀገ​ራ​ች​ንን ሊሰ​ልሉ ወደ​ዚህ በሌ​ሊት ገቡ” ብለው ነገ​ሩት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለኢያሪኮም ንጉሥ፣ “እነሆ፤ ምድሪቱን ሊሰልሉ ጥቂት እስራኤላውያን በሌሊት ወደዚህ መጥተዋል” ተብሎ ተነገረው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለኢያሪኮም ንጉሥ እንዲህ ተብሎ ተነገረው፦ “እነሆ፥ ሰዎች ከእስራኤል ልጆች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“አገሪቱን ለመሰለል ከእስራኤላውያን መካከል ዛሬ ማታ ወደዚህ መጥተዋል” ተብሎ ለኢያሪኮ ንጉሥ ተነገረው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የኢያሪኮም ንጉሥ፦ እነሆ፥ ሰዎች ከእስራኤል ልጆች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ ሲባል ወሬ ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 2:2
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩት ሁሉ፥ በመ​ን​ገ​ዶ​ቹም የሚ​ሄዱ ብፁ​ዓን ናቸው።


ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።


ከጥ​ንት ጀምሮ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ እሠ​ራ​ለሁ፤ ወደ ኋላስ የሚ​መ​ልስ ማን ነው?


የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ፥ “ውጡና ምድ​ሪ​ቱን ኢያ​ሪ​ኮን እዩ” ብሎ ከሰ​ጢም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሰላ​ዮ​ችን በስ​ውር ላከ። እነ​ዚ​ያም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሄዱ፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ደረሱ፤ ረዓብ ወደ​ሚ​ሉ​አ​ትም ዘማ ቤት ገቡ፤ በዚ​ያም ዐደሩ።


የኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ፥ “ሀገ​ራ​ች​ንን ሁሉ ሊሰ​ልሉ መጥ​ተ​ዋ​ልና ወደ አንቺ የመ​ጡ​ትን በዚ​ችም ሌሊት ወደ ቤትሽ የገ​ቡ​ትን ሰዎች አውጪ በሉ​አት” ብሎ ወደ ረዓብ ላከ።


የዳ​ንም ልጆች ከወ​ገ​ና​ቸው አም​ስት ጽኑ​ዓን ሰዎች ምድ​ሪ​ቱን እን​ዲ​ሰ​ል​ሉና እን​ዲ​መ​ረ​ምሩ፥ “ሂዱ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሰልሉ” ብለው ከሶ​ራ​ሕና ከኢ​ስ​ታ​ሔል ላኩ። እነ​ዚ​ያም ወደ ተራ​ራ​ማዉ ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት መጥ​ተው በዚያ አደሩ።