አሁንም፥ በእግዚአብሔር ማሉልኝ፤ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንደ አደረግሁ እናንተ ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት እንድታደርጉ፥ በእውነት ምልክት ስጡኝ።
ኢያሱ 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአባቴን ቤት፥ እናቴንም፥ ወንድሞቼንና ቤቴንም ሁሉ፥ ያላቸውንም ሁሉ አድኑ፤ ሰውነታችንንም ከሞት አድኑ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአባቴንና የእናቴን፣ የወንድሞቼንና የእኅቶቼን እንዲሁም የእነርሱ የሆነውን ነፍስ ሁሉ እንድታተርፉልኝ፤ ከሞትም አድኑን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቴንና እናቴንም ወንድሞቼንና እኅቶቼንም ያላቸውንም ሁሉ አድኑ፥ ነፍሳችንንም ከሞት ታደጉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቴንና እናቴን፥ ወንድሞቼን፥ እኅቶቼንና የእነርሱን ቤተሰቦች ሁሉ ከሞት ለማዳን ቃል ግቡልኝ!” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቴንና እናቴንም ወንድሞቼንና እኅቶቼንም ያላቸውንም ሁሉ እንድታድኑ፥ ሰውነታችንንም ከሞት እንድታድኑ። |
አሁንም፥ በእግዚአብሔር ማሉልኝ፤ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንደ አደረግሁ እናንተ ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት እንድታደርጉ፥ በእውነት ምልክት ስጡኝ።
ሰዎቹም፥ “ሕይወታችንን ስለ እናንተ አሳልፈን ለሞት እንሰጣለን” አሉ፤ እርስዋም አለች፥ “እግዚአብሔር ምድሪቱን በሰጣችሁ ጊዜ ቸርነትንና ጽድቅን ታደርጉልናላችሁ።” ሰዎቹም፥ “ይህን ነገራችንን ባትገልጪ እግዚአብሔር ሀገራችሁን በእውነት አሳልፎ ከሰጠን ከአንቺ ጋር ቸርነትን እናደርጋለን” አሏት።
እነዚያም ከተማዪቱን የሰለሉ ሁለቱ ጐልማሶች ወደ ዘማዪቱ ረዓብ ቤት ገብተው ረዓብን፥ አባቷንና እናቷን፥ ወንድሞችዋንም፥ ያላትንም ሁሉ፥ ቤተ ዘመዶችዋንም ሁሉ አወጡአቸው፤ ከእስራኤልም ሰፈር በውጭ አስቀመጡአቸው።