ኢያሱ 19:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለተኛውም ዕጣ ለስምዖን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ ርስታቸውም በይሁዳ ልጆች ርስት መካከል ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለተኛው ዕጣ ለስምዖን ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤ ርስታቸውም ዙሪያውን በይሁዳ ነገድ ርስት የተከበበ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለተኛውም ዕጣ ለስምዖን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ ርስታቸውም በይሁዳ ልጆች ርስት መከከል ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለተኛው ዕጣ ለስምዖን ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ ርስቱም ለይሁዳ ነገድ እስከ ተመደበው ምድር ድረስ ገባ ያለ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለተኛውም ዕጣ ለስምዖን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፥ ርስታቸውም በይሁዳ ልጆች ርስት መከከል ነበረ። |
በደቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉት የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ቤሴሌኤል፥ አራ፥ አሦር፤
ኢየሩሳሌም የምትባል የኢያቡሴዎን ከተማና የኢያሪሞን ከተማ ገባዖን፤ ዐሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፤ የይሁዳም ልጆች ዕድል ፋንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ።