የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 10:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው በፊ​ትህ የሚ​ተ​ርፍ የለም፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርም ኢያሱን፣ “አትፍራቸው፤ ሁሉንም አሳልፌ በእጅህ ሰጥቻቸዋለሁ፤ አንዳቸውም እንኳ ሊቋቋሙህ አይችሉም” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁና አትፍራቸው፤ ከእነርሱም አንድም ሰው የሚቋቋምህ የለም።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም ኢያሱን “እነርሱን አትፍራቸው፤ እኔ አንተን በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ ከእነርሱ አንድም የሚቋቋምህ አይኖርም” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁና አትፍራቸው፥ ከእነርሱም አንድ ሰው የሚቋቋምህ የለም አለው።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 10:8
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁለ​ቱም የዐ​መፅ ልጆች የሆኑ ሰዎች ገብ​ተው በፊቱ ቆሙ፤ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሡን ሰድ​በ​ሃል” ብለው መሰ​ከ​ሩ​በት። የዚያ ጊዜም ከከ​ተማ አው​ጥ​ተው በድ​ን​ጋይ ደብ​ድ​በው ገደ​ሉት።


እን​ግ​ዲህ ስለ​ዚህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይች​ለ​ናል?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​አ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራው፤ በሐ​ሴ​ቦን ይኖር በነ​በ​ረው በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ በሴ​ዎን ላይ እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ በእ​ር​ሱም ታደ​ር​ግ​በ​ታ​ለህ አለኝ።


ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ስማ​ቸ​ው​ንም ከዚያ ቦታ ያጠ​ፋል፤ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ ማንም ከፊ​ትህ ይቆም ዘንድ አይ​ች​ልም።


ኢያ​ሱም፥ “በም​ት​ወ​ጉ​አ​ቸው በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ሁሉ ላይ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ር​ጋ​ልና አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግጡ፤ ጽኑ፤ አይ​ዞ​አ​ችሁ” አላ​ቸው።


ኢያ​ሱም ከጌ​ል​ገላ ሌሊ​ቱን ሁሉ ገሥ​ግሦ በድ​ን​ገት ደረ​ሰ​ባ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ይሞቱ ዘንድ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን ቋንጃ ትቈ​ር​ጣ​ለህ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግጥ፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችን ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤ ተነ​ሥ​ተ​ህም ወደ ጋይ ውጣ፤ እነሆ፥ የጋ​ይ​ንም ንጉሥ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ከተ​ማ​ው​ንም ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ምድ​ያ​ም​ንም እንደ አንድ ሰው አድ​ር​ገህ ታጠ​ፋ​ለህ” አለው።


በዚ​ያ​ችም ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሰፈር ውረድ።


ይህም ጉባኤ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ይ​ፍና በጦር የሚ​ያ​ድን እን​ዳ​ይ​ደለ ያው​ቃል። ሰልፉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እና​ን​ተን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።”