የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 43:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይሁ​ዳም እን​ዲህ አለው፥ “የሀ​ገሩ ጌታ ያ ሰው፦ ‘ወን​ድ​ማ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር ከአ​ል​መጣ ፊቴን አታ​ዩም’ ብሎ በም​ስ​ክር ፊት አዳ​ኝ​ቶ​ብ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይሁዳ ግን እንዲህ አለው፤ “ያ ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎ በጥብቅ አስጠንቅቆናል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይሁዳ ግን እንዲህ አለው፤ “ያ ሰው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎ በጥብቅ አስጠንቅቆናል፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይሁዳ ግን ለአባቱ እንዲህ ብሎ መለሰለት፥ “ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ እፊቴ እንዳትቀርቡ’ በማለት በብርቱ አስጠንቅቆናል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይሁዳም እንዲህ አለው፦ ያ ሰው፦ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልሆነ ፊቴን አታዪም ብሎ በብርቱ ቃል አስጠነቀቀን።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 43:3
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከግ​ብ​ፅም ያመ​ጡ​ትን እህል በል​ተው ከፈ​ጸሙ በኋላ አባ​ታ​ቸው፥ “እን​ደ​ገና ሂዱ፤ ጥቂት እህል ሸም​ታ​ችሁ አም​ጡ​ልን” አላ​ቸው።


ወን​ድ​ማ​ች​ንን ከእኛ ጋር ብት​ል​ከው እን​ወ​ር​ዳ​ለን፤ እህ​ልም እን​ሸ​ም​ት​ል​ሃ​ልን፤


ወን​ድ​ማ​ች​ንን ከእኛ ጋር ባት​ል​ከው ግን አን​ሄ​ድም፤ ያ ሰው ‘ታናሽ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ ጋር ካላ​መ​ጣ​ችሁ ፊቴን አታ​ዩም’ ብሎ​ና​ልና።”


አንተ ጌታ​ች​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን፦ ታናሽ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ ጋር ከአ​ላ​መ​ጣ​ች​ሁት ዳግ​መኛ ፊቴን አታ​ዩም አል​ኸን።


ንጉ​ሡም፥ “ወደ ቤቱ ይሂድ እንጂ ፊቴን እን​ዳ​ያይ” አለ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ፊት አላ​የም።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀ​መጠ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ፊት አላ​የም።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኢዮ​አ​ብን፥ “ከጌ​ድ​ሶር ለምን መጣሁ? በዚ​ያም ተቀ​ምጬ ቢሆን ይሻ​ለኝ ነበር ብለህ እን​ድ​ት​ነ​ግ​ረው ወደ ንጉሥ እል​ክህ ዘንድ ወደ እኔ ና ብዬ ወደ አንተ ላክሁ፤ አሁ​ንም የን​ጉ​ሡን ፊት አላ​የ​ሁም፤ ኀጢ​አት ቢኖ​ር​ብኝ ይግ​ደ​ለኝ” አለው።


ዳዊ​ትም፥ “ይሁን፤ በመ​ል​ካም ፈቃ​ደ​ኛ​ነት ከአ​ንተ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር ከአ​ንተ እሻ​ለሁ፤ ፊቴን ለማ​የት በመ​ጣህ ጊዜ፥ የሳ​ኦ​ልን ልጅ ሜል​ኮ​ልን ካላ​መ​ጣ​ህ​ልኝ ፊቴን አታ​ይም” አለው።


አሁ​ንም እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት የሰ​በ​ክ​ሁ​ላ​ችሁ እና​ንተ ሁላ​ችሁ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ፊቴን እን​ደ​ማ​ታ​ዩኝ እኔ ዐው​ቄ​አ​ለሁ።


ይል​ቁ​ንም “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ፊቴን አታ​ዩ​ትም” ስለ አላ​ቸው እጅግ አዘኑ። እስከ መር​ከ​ብም ድረስ ሸኙት።


በግ​ብፅ ያሉ​ትን የወ​ገ​ኖ​ችን መከራ ማየ​ትን አይ​ቻ​ለሁ፤ ጩኸ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰም​ቻ​ለሁ፤ ላድ​ና​ቸ​ውም ወር​ጃ​ለሁ፤ አሁ​ንም ና ወደ ግብፅ ሀገር ልላ​ክህ።’