የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ቀን ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈራና፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ እኔ እን​ዴት ትገ​ባ​ለች?” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊት በዚያ ቀን እግዚአብሔርን ስለ ፈራ “የእግዚአብሔር ታቦት እንዴት ወደ እኔ ይመጣል?” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊት በዚያን ቀን ጌታን ስለ ፈራ “የጌታ ታቦት እንዴት ወደ እኔ ይመጣል?” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያም በኋላ ዳዊት እግዚአብሔርን ስለ ፈራ “እንዲህ ከሆነማ የቃል ኪዳኑን ታቦት እንዴት ልወስደው እችላለሁ?” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያም ቀን ዳዊት እግዚአብሔርን ፈራና፦ የእግዚአብሔር ታቦትም ወደ እኔ እንዴት ይመጣል? አለ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 6:9
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዖዛን ስለ ገደ​ለው ዳዊት አዘነ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የዚያ ስፍራ ስም “ዖዛ የሞ​ተ​በት” ተባለ።


“በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው ጋር በም​ድር ላይ ይኖ​ራ​ልን? እነሆ ሰማይ ከሰ​ማ​ያ​ትም በላይ ያለው ሰማይ ይይ​ዝህ ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ይል​ቁ​ንስ እኔ ለስ​ምህ የሠ​ራ​ሁት ቤት እን​ዴት ያንስ!


እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።


ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ፤’ አለ።


እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፥ ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ።


የቤ​ት​ሳ​ሚ​ስም ሰዎች፥ “በዚህ በቅ​ዱሱ አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ማለፍ ማን ይች​ላል? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ከእኛ ወጥታ ወደ ማን ትሄ​ዳ​ለች?” አሉ።