የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 24:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ጤሮ​ስም ምሽግ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ከተ​ሞች ሁሉ መጡ፤ በይ​ሁ​ዳም ደቡብ በኩል በቤ​ር​ሳ​ቤህ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደግሞም ወደ ጢሮስ ምሽግ፣ ወደ ኤዊያውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች፣ በመጨረሻም በይሁዳ ደቡብ ወዳለችው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያ ወደ ጢሮስ ምሽግ፥ ወደ ሒዋውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች፥ በይሁዳ ደቡብ ወዳለችው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀጥሎም በደቡብ በኩል ወደተመሸገችው ወደ ጢሮስ ከተማና እንዲሁም ወደ ሒዋውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች ሁሉ ሄዱ፤ በመጨረሻም በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህ ዘለቁ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ጢሮስም ምሽግ ወደ ኤዊያውያንና ወደ ከነዓናውያንም ከተሞች ሁሉ መጡ፥ በይሁዳም ደቡብ በኩል በቤርሳቤህ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 24:7
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ረ​ውን የሠ​ራ​ዊት አለቃ ኢዮ​አ​ብን፥ “የሕ​ዝ​ቡን ድምር አውቅ ዘንድ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ሂድ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ቍጠ​ራ​ቸው” አለው።


በሀ​ገ​ሪ​ቱም ሁሉ ላይ ተመ​ላ​ል​ሰው ከዘ​ጠኝ ወርና ከሃያ ቀን በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።


ጢሮስም ምሽግን ለራስዋ ሠርታለች፥ ብሩንም እንደ አፈር ጥሩውንም ወርቅ እንደ መንገድ ጭቃ አከማችታለች።


በም​ሥ​ራ​ቃዊ ባሕር ዳርቻ ወዳ​ለው ወደ ከነ​ዓ​ና​ዊው፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር ወዳ​ለው ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊው፥ በቆ​ላ​ማ​ውና በመ​ሴፋ ወዳ​ለው ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ዉም ላከ።


ከዚ​ያም ወደ ኤብ​ሮን፥ ወደ ረዓብ፥ ወደ አሜ​ማ​ህን፥ ወደ ቀን​ታን እስከ ታላቁ ሲዶና ይደ​ር​ሳል።


ድን​በ​ሩም ወደ ራማ፥ ወደ መስ​ፋጥ ምንጭ ወደ ጢሮስ ይዞ​ራል፤ ድን​በ​ሩም ወደ ኢያ​ሴፍ ይዞ​ራል፤ መው​ጫ​ውም በሌ​ብና በኮ​ዛብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በተ​ራ​ራ​ማው በሜ​ዳ​ውም በታ​ላቁ ባሕር ዳር በሊ​ባ​ኖ​ስም ፊት ለፊት የነ​በሩ ነገ​ሥት ሁሉ፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊዉ፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ዉም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ዉም ይህን በሰሙ ጊዜ፥


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን፥ “ምና​ል​ባት በመ​ካ​ከ​ላ​ችን የም​ት​ቀ​መጡ እንደ ሆነ እን​ዴ​ትስ ከእ​ና​ንተ ጋር ቃል ኪዳን እና​ደ​ር​ጋ​ለን?” አሉ​አ​ቸው።


እነ​ር​ሱም አም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መኳ​ን​ንት፥ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከበ​ዓ​ል​ሄ​ር​ሞን ተራራ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ በሊ​ባ​ኖስ ተራራ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፤