2 ሳሙኤል 17:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኩሲም ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፥ “አኪጦፌል ያለው ይህ ነው፤ ነገሩን እናደርገው ዘንድ ይገባልን? ባይሆን ግን አንተ ንገረን” ብሎ ተናገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኩሲ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፣ “አኪጦፌል ይህን ምክር አቅርቧል፤ ታዲያ እርሱ ያለውን እናድርግ? ካልሆነም እስኪ የአንተን ሐሳብ ንገረን” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሑሻይም ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፥ “አኪጦፌል ይህን ምክር አቅርቧል፤ ታዲያ የእርሱን ምክር እንከተል? ካልሆነ እስቲ አንተ ተናገር” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሑሻይም በደረሰ ጊዜ አቤሴሎም “አኪጦፌል የሰጠን ምክር ይህ ነው፤ ይህንኑ ምክር እንከተል ወይስ ምን ማድረግ እንደሚገባን አንተም የምትነግረን አለ ይሆን?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኩሲም ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፦ አኪጦፌል ያለው ይህ ነው፥ ነገሩን እናደርገው ዘንድ ይገባልን? ባይሆን ግን አንተ ንገረን ብሎ ተናገረው። |