2 ሳሙኤል 17:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ሑሻይም በደረሰ ጊዜ አቤሴሎም “አኪጦፌል የሰጠን ምክር ይህ ነው፤ ይህንኑ ምክር እንከተል ወይስ ምን ማድረግ እንደሚገባን አንተም የምትነግረን አለ ይሆን?” ሲል ጠየቀው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ኩሲ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፣ “አኪጦፌል ይህን ምክር አቅርቧል፤ ታዲያ እርሱ ያለውን እናድርግ? ካልሆነም እስኪ የአንተን ሐሳብ ንገረን” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ሑሻይም ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፥ “አኪጦፌል ይህን ምክር አቅርቧል፤ ታዲያ የእርሱን ምክር እንከተል? ካልሆነ እስቲ አንተ ተናገር” አለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ኩሲም ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፥ “አኪጦፌል ያለው ይህ ነው፤ ነገሩን እናደርገው ዘንድ ይገባልን? ባይሆን ግን አንተ ንገረን” ብሎ ተናገረው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ኩሲም ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፦ አኪጦፌል ያለው ይህ ነው፥ ነገሩን እናደርገው ዘንድ ይገባልን? ባይሆን ግን አንተ ንገረን ብሎ ተናገረው። ምዕራፉን ተመልከት |