2 ሳሙኤል 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም፥ “ነገሩ ምንድን ነው? እስኪ ንገረኝ” አለው። እርሱም መልሶ፥ “ሕዝቡ ከሰልፉ ሸሽቶአል፤ ከሕዝቡም ብዙው ወደቁ፤ ሞቱም፤ ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ደግሞ ሞተዋል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም፣ “ምን ነገር ተፈጠረ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “ሰዎቹ ከጦርነቱ ሸሽተዋል፤ ብዙዎቹ ወድቀዋል፤ ሞተዋል፤ ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም፥ “እስቲ ምን ነገር እንደተፈጠረ ንገረኝ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “ሰዎቹ ከጦርነቱ ሸሽተዋል፤ ብዙዎቹ ወድቀዋል፤ ሞተዋልም፤ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “እስቲ የሆነውን ሁሉ ንገረኝ” አለው። እርሱም “ሠራዊታችን ከጦር ግንባር ሸሸ፤ ከሰዎቻችንም ብዙዎቹ ሞቱ፤ ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም፦ ነገሩ እንደ ምን ሆነ? እስኪ ንገረኝ አለው። እርሱም መልሶ፦ ሕዝቡ ከሰልፉ ሸሽቶአል፥ ከሕዝቡ ብዙው ወደቁ ሞቱም፥ ሳኦልና ልጁም ዮናታን ደግሞ ሞተዋል አለ። |
ሰውዬውንም፥ “አንተ ከወዴት ነህ?” አለው። እርሱም፥ “ጦርነቱ ከአለበት ስፍራ የመጣሁ እኔ ነኝ፥ ዛሬም ከሰልፍ ሸሸሁ” አለ። እርሱም፥ “ልጄ ሆይ! ነገሩስ እንዴት ሆነ?” አለው።