እርሱ ግን የኢሎፍሊንና የሞዓብን፥ የምድያምንና የሶርያን፥ የግብፅንም ሕዝብ ያስነሣባቸው ነበር፤ ጠላቶቻቸውም ድል በነሷቸው ጊዜ፥ መከራ በአጸኑባቸውና በአስገበሯቸው ጊዜ፥ በገዟቸውም ጊዜ ይጮሁና ያለቅሱ ነበር፤ እግዚአብሔርም በወደደበት ጊዜ ያድኗቸው ዘንድ መሳፍንትን ያስነሣላቸው ነበር፤ መሳፍንቱም ያድኗቸው ነበር።