የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 27:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ስድ​ስቱ መቶ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አሜህ ልጅ ወደ አን​ኩስ አለፉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ዳዊትና ዐብረውት ያሉት ስድስት መቶ ሰዎች ተነሥተው የጋት ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ አሜህ ልጅ ወደ አንኩስ ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ ዳዊትና አብረውት ያሉት ስድስት መቶ ሰዎች ተነሥተው የጋት ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ማዖክ ልጅ ወደ አኪሽ ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም ዳዊትና ስድስት መቶ ተከታዮቹ ወዲያውኑ ተነሥተው የጋት ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ማዖክ ልጅ ወደ አኪሽ ሄዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም ከእርሱም ጋር የነበሩት ስድስቱ መቶ ሰዎች ተነሥተው ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አሜህ ልጅ ወደ አንኩስ አለፉ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 27:2
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሴ​ቅ​ላ​ቅም ከቂስ ልጅ ከሳ​ኦል በተ​ሸ​ሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት የመጡ እነ​ዚህ ናቸው፤ በጦ​ር​ነ​ትም ባገ​ዙት ኀያ​ላን መካ​ከል ነበሩ።


ዳዊ​ትም ተነሣ በዚ​ያም ቀን ከሳ​ኦል ፊት ሸሸ፤ ወደ ጌትም ንጉሥ ወደ አን​ኩስ መጣ።


የአ​ን​ኩስ ብላ​ቴ​ኖ​ችም፥ “ይህ ዳዊት የሀ​ገሩ ንጉሥ አይ​ደ​ለ​ምን? ሳኦል ሺህ፥ ዳዊ​ትም ዐሥር ሺህ ገደለ ብለው ሴቶች በዘ​ፈን የዘ​መ​ሩ​ለት እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?” አሉት።


ዳዊ​ትም ሰዎ​ቹን፥ “ሁላ​ችሁ ሰይ​ፋ​ች​ሁን ታጠቁ” አላ​ቸው። ሁሉም ሰይ​ፋ​ቸ​ውን ታጠቁ፤ ዳዊ​ትም ሰይ​ፉን ታጠቀ፤ አራት መቶ ሰዎ​ችም ዳዊ​ትን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ሁለት መቶ​ውም በጓ​ዛ​ቸው ዘንድ ተቀ​መጡ።


ዳዊ​ትም፥ “የእ​ነ​ዚ​ህን ሠራ​ዊት ፍለጋ ልከ​ተ​ልን? አገ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ሁን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እር​ሱም፥ “ታገ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ህና፥ ፈጽ​መ​ህም ምር​ኮ​ኞ​ቹን ታድ​ና​ለ​ህና ፍለ​ጋ​ቸ​ውን ተከ​ተል” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ዳዊ​ትም ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ስድ​ስት መቶ ሰዎች ሄዱ፤ እስከ ቦሦር ወንዝ ድረ​ስም መጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የቀ​ሩት በዚያ ተቀ​መጡ።