Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 25:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዳዊ​ትም ሰዎ​ቹን፥ “ሁላ​ችሁ ሰይ​ፋ​ች​ሁን ታጠቁ” አላ​ቸው። ሁሉም ሰይ​ፋ​ቸ​ውን ታጠቁ፤ ዳዊ​ትም ሰይ​ፉን ታጠቀ፤ አራት መቶ ሰዎ​ችም ዳዊ​ትን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ሁለት መቶ​ውም በጓ​ዛ​ቸው ዘንድ ተቀ​መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዳዊትም ሰዎቹን፣ “በሉ ሁላችሁም ሰይፋችሁን ታጠቁ” አላቸው። ስለዚህ ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፤ ዳዊትም የራሱን ታጠቀ። አራት መቶ ያህል ሰዎች ከዳዊት ጋራ ሲወጡ መቶ ያህሉ ግን ጓዝ ለመጠበቅ ቀሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዳዊትም ሰዎቹን፥ “በሉ ሁላችሁም ሰይፋችሁን ታጠቁ” አላቸው። ስለዚህ ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፤ ዳዊትም የራሱን ታጠቀ። አራት መቶ ያህል ሰዎች ከዳዊት ጋር ሲወጡ መቶ ያህሉ ግን ጓዝ ለመጠበቅ ቀሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ዳዊትም “በሉ ሰይፋችሁን ታጠቁ!” የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም እንደ ታዘዙት አደረጉ፤ ዳዊትም ራሱ ሰይፉን ታጠቀ፤ ጓዝ የሚጠብቁ ሁለት መቶ ሰዎች ወደ ኋላ ትቶ አራት መቶ ሰዎች በማስከተል ገሥግሦ ለመሄድ ተነሣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዳዊትም ሰዎቹን፦ ሁላችሁ ሰይፋችሁን ታጠቁ አላቸው። ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፥ ዳዊትም ሰይፉን ታጠቀ፥ አራት መቶ ሰዎችም ዳዊትን ተከትለው ወጡ፥ ሁለት መቶውም በዕቃው ዘንድ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 25:13
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትና ስድ​ስት መቶ የሚ​ሆኑ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ከቂ​አላ ወጡ፤ ወደ​ሚ​ሄ​ድ​በ​ትም ይከ​ተ​ሉት ነበር። ሳኦ​ልም ዳዊት ከቂ​አላ እንደ ሸሸ ሰማ፤ ስለ​ዚ​ህም ከመ​ው​ጣት ቀረ።


ይቅር ባይ ሰው ይታገሣል፥ መመካቱም ኀጢአተኞችን ይቃወማቸዋል፥


ነፍስ ዕውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል።


ትዕግሥተኛ ሰው ጥበብ የበዛለት ይሆናል፤ ትዕግሥት የጐደለው ሰው ግን ሰነፍ ነው፤


አለ​ቆ​ችም ከስ​ን​ቃ​ቸው ወሰዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ጠ​የ​ቁም።


ትዕግሥተኛ ሰው ከኀያል፥ ጥበብ ያለው ሰውም ሰፊ ርስት ካለው፥ በመንፈሱ የሠለጠነ ሰውም ሀገርን ከሚገዛ ሰው ይሻላል።


የተ​ጨ​ነ​ቀም ሁሉ፥ ዕዳም ያለ​በት ሁሉ፥ የተ​ከ​ፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​ባ​ሰበ፤ እር​ሱም በላ​ያ​ቸው አለቃ ሆነ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።


የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች ዞረው በመ​ጡ​በት መን​ገድ ተመ​ለሱ፤ መጥ​ተ​ውም ይህን ነገር ሁሉ ለዳ​ዊት ነገ​ሩት።


ዳዊ​ትም ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ስድ​ስቱ መቶ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አሜህ ልጅ ወደ አን​ኩስ አለፉ።


ብላ​ቴ​ኖ​ቹም ሁሉ ተከ​ተ​ሉት፤ ኬል​ቲ​ያ​ው​ያ​ንና ፌል​ታ​ው​ያ​ንም ሁሉ በም​ድረ በዳ በወ​ይራ ሥር ቆሙ። ሕዝ​ቡም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ይሄዱ ነበር። ከእ​ርሱ ጋር ያሉ ሰዎ​ችም ሁሉ ስድ​ስት መቶ ነበሩ። ከእ​ርሱ ጋር ፌል​ታ​ው​ያ​ንና ኬል​ቲ​ያ​ው​ያን፥ በእ​ግ​ራ​ቸው ከጌት የመጡ ስድ​ስት መቶ ጌታ​ው​ያ​ንም ነበሩ። በን​ጉ​ሡም ፊት ይሄዱ ነበር።


ጠላቴን እበቀለዋለሁ አትበል፤ ነገር ግን እንዲረዳህ እግዚአብሔርን ተማመን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች