የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 10:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በአ​ንተ ይወ​ር​ዳል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ትን​ቢት ትና​ገ​ራ​ለህ፤ እንደ ሌላም ሰው ሆነህ ትለ​ወ​ጣ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔር መንፈስ በኀይል ይወርድብሃል፤ ከእነርሱ ጋራ ትንቢት ትናገራለህ፤ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጌታም መንፈስ በኃይል ይወርድብሃል፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፤ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በድንገት የእግዚአብሔር መንፈስ በአንተ ላይ በኀይል ይወርዳል፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት መናገር ትጀምራለህ፤ ልዩ ሰውም ትሆናለህ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ይወርድብሃል፥ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 10:6
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔም እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ያም አነ​ጋ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ በአ​ንተ ካለ​ውም መን​ፈስ ወስጄ በእ​ነ​ርሱ ላይ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ብቻ እን​ዳ​ት​ሸ​ከም የሕ​ዝ​ቡን ሸክም ከአ​ንተ ጋር ይሸ​ከ​ማሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​መ​ናው ወረደ፤ ተና​ገ​ረ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ላይ ከነ​በ​ረው መን​ፈስ ወስዶ በሰ​ባው ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ላይ አደ​ረገ፤ መን​ፈ​ሱም በላ​ያ​ቸው ባደረ ጊዜ ትን​ቢት ተና​ገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን አል​ተ​ጨ​መ​ረ​ላ​ቸ​ውም።


ከእ​ነ​ር​ሱም ሁለት ሰዎች በሰ​ፈር ቀር​ተው ነበር፤ የአ​ን​ዱም ስም ኤል​ዳድ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ሞዳድ ነበረ፤ መን​ፈ​ስም ዐረ​ፈ​ባ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ከተ​ጻ​ፉት ጋር ነበሩ፤ ወደ ድን​ኳኑ ግን አል​ወ​ጡም ነበር፤ በሰ​ፈ​ሩም ውስጥ ትን​ቢት ተና​ገሩ።


ሙሴም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ሁሉ ነቢ​ያት ቢሆኑ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሱን ቢያ​ሳ​ድር አንተ ስለ እኔ ትቀ​ና​ለ​ህን?” አለው።


በዚያ ቀን ብዙዎች ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን?’ ይሉኛል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ የፍ​የል ጠቦ​ትን እን​ደ​ሚ​ጥ​ልም ጣለው፤ በእ​ጁም እንደ ኢም​ንት ሆነ፤ ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ለአ​ባ​ቱና ለእ​ናቱ አል​ተ​ና​ገ​ረም።


የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ወደ ተባለ ቦታም ደረሰ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ደን​ፍ​ተው ተቀ​በ​ሉት፤ ወደ እር​ሱም ሮጡ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ በክ​ን​ዱም ያሉ እነ​ዚያ ገመ​ዶች በእ​ሳት ላይ እንደ ተጣለ ገለባ ሆኑ፤ ማሰ​ሪ​ያ​ውም ከክ​ንዱ ተፈታ፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ይፈ​ርድ ነበር፤ ለጦ​ር​ነ​ትም ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በወ​ን​ዞች መካ​ከል ያለች የሶ​ርያ ንጉሥ ኩሳ​ር​ሳ​ቴ​ምን በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም ላይ በረ​ታች።


ወደ​ዚ​ያም ኮረ​ብታ በደ​ረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነ​ቢ​ያት ጉባኤ አገ​ኙት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ ወረደ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ትን​ቢት ተና​ገረ።


ከሳ​ሙ​ኤ​ልም ዘንድ ለመ​ሄድ ፊቱን በመ​ለሰ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሌላ ልብ ለወ​ጠ​ለት፤ በዚ​ያም ቀን እነ​ዚህ ምል​ክ​ቶች ሁሉ ደረ​ሱ​ለት።


ይህ​ንም ነገር በሰማ ጊዜ በሳ​ኦል ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ መጣ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ተቈጣ።


ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቀባው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳ​ዊት ላይ መጣ። ሳሙ​ኤ​ልም ተነ​ሥቶ ወደ አር​ማ​ቴም ሄደ።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ያመ​ጡት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ የነ​ቢ​ያ​ት​ንም ጉባኤ አገኙ፤ ሳሙ​ኤ​ልም አለ​ቃ​ቸው ሆኖ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆሞ ነበረ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በሳ​ኦል መል​እ​ክ​ተ​ኞች ላይ ወረደ፤ እነ​ር​ሱም ትን​ቢት ይና​ገሩ ጀመር።