Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 10:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እነ​ዚ​ህም ምል​ክ​ቶች በደ​ረ​ሱህ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና እጅህ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ አድ​ርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እነዚህ ምልክቶች በተፈጸሙ ጊዜ እጅህ ማድረግ የምትችለውን ሁሉ አድርግ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እነዚህ ምልክቶች በተፈጸሙ ጊዜ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና እጅህ ማድረግ የምትችለውን ሁሉ አድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እነዚህም ምልክቶች በተፈጸሙ ጊዜ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለ ሆነ ማድረግ የሚገባህን ሁሉ አድርግ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እነዚህም ምልክቶች በደረሱህ ጊዜ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና እጅህ የምታገኘውን ሁሉ አድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 10:7
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዚያ ሕፃን ጋር ነበረ፤ አደ​ገም፤ በም​ድረ በዳም ተቀ​መጠ፤ ቀስ​ተ​ኛም ሆነ።


ናታ​ንም ንጉ​ሡን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና፥ ሂድና በል​ብህ ያሰ​ብ​ኸ​ውን ሁሉ አድ​ርግ” አለው።


ሀብቴ በበዛ ጊዜ፥ ደስ ብሎኝ እንደ ሆነ፥ ስፍር ቍጥር በሌ​ለ​ውም መዝ​ገብ ላይ እጄን ጨምሬ እንደ ሆነ፥


ደግ​ሞም አለው፥ “እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ባያ​ም​ኑህ፥ በፊ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ምል​ክት ቃል​ህን ባይ​ሰሙ፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪቱ ምል​ክት ቃል​ህን ያም​ናሉ።


አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።


ስለ​ዚህ ጌታ ራሱ ምል​ክት ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እነሆ፥ ድን​ግል ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ዳ​ለች፤ ስሙ​ንም አማ​ኑ​ኤል ብላ ትጠ​ራ​ዋ​ለች።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።


ለእ​ና​ን​ተም ምል​ክቱ እን​ዲህ ነው፦ ሕፃን አውራ ጣቱን ታስሮ፥ በጨ​ር​ቅም ተጠ​ቅ​ልሎ በበ​ረት ውስጥ ተኝቶ ታገ​ኛ​ላ​ቸሁ።”


ሕዝ​ቡም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት አይ​ተው፥ “ይህ በእ​ው​ነት ወደ ዓለም የሚ​መ​ጣው ነቢይ ነው” አሉ።


“ጠላ​ቶ​ች​ህን ለመ​ው​ጋት በወ​ጣህ ጊዜ፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ሕዝ​ቡ​ንም ከአ​ንተ ይልቅ በዝ​ተው ባየህ ጊዜ፥ ከግ​ብፅ ሀገር ያወ​ጣህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና አት​ፍ​ራ​ቸው።


ገን​ዘብ ሳት​ወዱ ኑሩ፤ ያላ​ች​ሁም ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ እርሱ “አል​ጥ​ል​ህም፤ ቸልም አል​ል​ህም” ብሎ​አ​ልና።


በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ የሚ​ቋ​ቋ​ምህ የለም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበ​ርሁ እን​ዲሁ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ አል​ጥ​ል​ህም፥ ቸልም አል​ል​ህም።


እነሆ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አት​ፍራ፥ አት​ደ​ን​ግ​ጥም።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለእ​ርሱ ተገ​ልጦ፥ “አንተ ጽኑዕ ኀያል ሰው! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው” አለው።


ነገም ፀሐይ በወ​ጣች ጊዜ ማል​ደህ ተነሣ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ክበ​ባት፤ እነ​ሆም፥ እር​ሱና ከእ​ርሱ ጋር ያሉት ሕዝብ በአ​ንተ ላይ በወጡ ጊዜ እጅህ እን​ዳ​ገ​ኘች አድ​ር​ግ​በት።”


ይህ በሁ​ለቱ ልጆ​ችህ በአ​ፍ​ኒ​ንና በፊ​ን​ሐስ ላይ የሚ​መጣ ለአ​ንተ ምል​ክት ነው፤ ሁለቱ በአ​ንድ ቀን በጦር ይሞ​ታሉ።


አባ​ቴም በአ​ንተ ላይ ክፋት ማድ​ረግ ቢወ​ድድ፥ እኔም ባላ​ስ​ታ​ው​ቅህ፥ በሰ​ላ​ምም ትሄድ ዘንድ ባላ​ሰ​ና​ብ​ትህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዮ​ና​ታን ይህን ያድ​ርግ፤ ይህ​ንም ይጨ​ምር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን።


ሳሙ​ኤ​ልም አደገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ከቃ​ሉም አን​ዳች በም​ድር ላይ አይ​ወ​ድ​ቅም ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች