ኢያሱ 3:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢያሱ እስራኤላውያንን፦ “ወደዚህ ቅረቡና የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አድምጡ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱ የእስራኤልን ሕዝብ “ወደዚህ ቀርባችሁ፣ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ አላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ለእስራኤል ልጆች፦ “ወደዚህ ቀርባችሁ የአምላካችሁን የጌታን ቃላት ስሙ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ለእስራኤል ልጆች፥ “ወደዚህ ቀርባችሁ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ለእስራኤል ልጆች፦ ወደዚህ ቀርባችሁ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ አለ። |
ከዚህ በኋላ ሙሴ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “እስራኤል ሆይ፥ አሁን እንግዲህ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ ለመውረስ ያበቃችሁ ዘንድ የማስተምራችሁን ሕግና ሥርዓት አዳምጣችሁ በሥራ ላይ አውሉት።
ኢያሱም ንግግሩን በመቀጠል፦ “ሕያው እግዚአብሔር በመካከላችሁ መሆኑን የምታውቁት እናንተ ወደ ፊት እየገፋችሁ በሄዳችሁ መጠን እርሱ ከነዓናውያንን፥ ሒታውያንን፥ ሒዋውያንን፥ ፈሪዛውያንን፥ ጌርጌሳውያንን፥ አሞራውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ የሚያስወጣ በመሆኑ ነው።
የቃል ኪዳኑን ታቦት ለሚሸከሙት ካህናት፦ ‘ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ በምትደርሱበት ጊዜ በወንዙ ውስጥ ቀጥ ብላችሁ ቁሙ’ ብለህ ንገራቸው።”