ሕፃናትን የሚገድሉ ምሕረት የለሾች፥ በበዓላት ላይ የሰውን ስጋና ደም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚበሉ ሰው በላዎች፥ የምሥጢራዊ ወንድማማችነት ምልምሎች፥
ያለርኅራኄም ልጆቻቸውን ስለመግደላቸው፥ የሰዎችን ሆድ ዕቃና ሥጋቸውን ለመብላት፥ ደማቸውንም ለመጠጣት ስለ መፍቀዳቸው ጠልተኻቸዋል። የጌትነትህን ምሥጢራት ማወቅ ከመካከላቸው ርቋልና።